Felegekin 6th stage 6ተኛው የፈለገኪን የኪነጥበብ መድረክ _ ደራሲና ገጣሚ ተስፋዬ ማሞና ኣንጋፋው የሙዚቃ ከያኒ አርቲስት ዳዊት ይፍሩ - ክፍል1

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 11 фев 2025
  • ተስፋችን በአንድነታችን እንዲሰምር፤ ኑ ሰላምን እንዘምር። እነሆ ጥበብ በጠቢባን ብትፈቀር፤ ኪነት በፈለገኪን እንድትሞሸር፤ ስድስተኛው የፈለገኪን የኪነጥበብ መድረክ መሰናዶውም ተጧጡፎ ጥር ሃያ አራት እለተቅዳሜ ማረፊያው ሆኗል።
    ደራሲ፣ ገጣሚ፣ መምህርና ተርጓሚ ዳኛቸው ወርቁ ስራዎቹና ህይወቱ በፈለገኪን በሚገባ ተዘክሯ።
    ትናንት እና ዛሬ ተዋዶ፤
    ዘመንና ትውልድም ተዋህዶ፤
    ፍቅር በጥበብ እንዲቃኝ፤
    መክሊት በኪነት በሚዳኝ፤
    እውነት በእምነት እንዲገኝ፤
    ደራሲና ገጣሚ ተስፋዬ ማሞና ኣንጋፋው የሙዚቃ ከያኒ አርቲስት ዳዊት ይፍሩ የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ ሆነውበታል። በእለቱ ከስምንት ሰአት ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጲያ አይነስውራን ብሄራዊ ማህበር ግቢ የፈለገኪን የኪነጥበብ ፕሮግራም ሲመደረክ፤ እንደቀደሙቱ (የፈለገኪን) መሰናዶዎች ሁሉ ዓይነስውራን ትንታግ ገጣሚያን፣ ደራሲያንና ድምጻዊያን ከአይናማ ወዳጆቻቸውጋር በወጋገን ባንድ ታጅበው በመድረኩ ነግሰውበታል።
    ** ታናናሾችን እያጀገንን ታላላቆችንም እንዲህ እናከብራለን። **

Комментарии •