ህፃናት ኪሎዋቸው እንዲጨምር ምን እናድርግ❓️ጤናማ የህፃናት የእድገት ክትትል ምንድነው❓️ ህፃናት እድገታቸው በምን ይለካል❓️
HTML-код
- Опубликовано: 7 фев 2025
- ልጅዎ በትክክል እያደገ መሆኑን አረጋግጠው ያውቃሉ❓️
ህፃናት #የጤና እና #የእድገት ክትትል መጀመር ያለባቸው ከመቼ ጀምሮ ነው ❓️👦👧
💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖
✔️ ህፃናት ገና ሳይታመሙ የእድገት ደረጃቸው እና የጤና ሁኔታቸው ለማወቅ ቋሚ የሆነ የጤና ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው::
✔️ ይህም ህፃናት ጤና እና እድገት ላይ ችግሮች በጣም ሳይባባሱ እና ጉዳት ሳያመጡ ቀድሞ ለመድረስ እና በሽታዎች ገና ሳይከሰቱ ከስር መሰረቱ ለመከላከል ይረዳል::
✔️ይህንን ለመርዳት ከተነደፉ መንገዶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው መንገድ #ጤናማ #የህፃናት #ክትትል(#Well #baby #clinic) ይባላል ::
✔️ ይህ አይነት ክትትል በሀገራችን ብዙ የተለመደ ባይሆንም በሌሎች ሃገራት ግን እጅግ የታወቀ እና ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር በመንግስት ደረጃ ድጋፍ የሚደረግለት ትልቅ የጤና መስክ ነው::
🛑 #ጤናማ #የህፃናት #ክትትል ላይ የሚታዩ እና የሚለኩ እና የሚደረጉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ❓️
👉 የህፃናትን አካላዊ እድገት( ክብደት፣ቁመት፣ የጭንቅላት መጠን እና የመሳሰሉት)
👉 ቀላል የሚመስሉ ግን ካልታከሙ ጉዳት የሚያመጡ ህመሞች ምርመራ ለምሳሌ:
📌 የደም ማነስ
📌 ማንኮራፋት
📌 ተደጋጋሚ የቶንስል እና የጆሮ ህመም
📌 ተደጋጋሚ የአንጀት እና የሆድ ህመሞች
📌 ኪሎ አለመጨመር ችግሮች እና የመሳሰሉት
👉 የምግብ ፍላጎት እና የአመጋገብ ችግሮች
👉 የሰውነት መዳበር እና እድገት
( Gross motor and fine motor development)
👉 አእምሮአዊ እድገት (Cognitive development)
👉 የቋንቋ እና የንግግር እድገት( Language development)
👉 ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ መስተጋብር እድገት (Psychosocial and communication)
👉 አካላዊ ምርመራ( Physical examination)
👉 የበሽታ ልየታና የጤና ቅኝት(Disease prevention and Health surveillance)
👉 ክትባትና የአደጋ ቅድመ ጥንቃቄ ትምህርት
🛑 #የጤናማ #የህፃናት #ክትትል(Well baby clinic) ጥቅሞች ምንድናቸው❓️
🔹ጤናማ የሆነ የህይወት ጅማሬ ይመሰርታል
🔹 የህፃናት ጤናማ እድገትን ያጎለብታል
🔹 የወላጆችን አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ይመልሳል
🔹 ለምሳሌ : ስለ ህፃናት እንቅልፍ ሰአት፣ ስለ አመጋገብ፣ ስለ ፀሐይ ማሞቅ እና የመሳሰሉት
🔹 በቤተሰብ ውስጥ የጤና እውቀትና ክህሎትን ያዳብራል
🔹 በወላጆችና ልጆች መካከል ጤናማ ግንኙነትን ያዳብራል
🔹 በሽታዎችን ከመሰረቱ ለማወቅና ለማከም ይረዳል
🔹 የጤና ወጪን ይቀንሳል
🔹 የአደጋ ቅድመ ጥንቃቄን በማስተማርና በማሳወቅ የህፃናትን ጉዳት/አደጋ ይቀንሳል
🔹 የህፃናት አካላዊ ፣አይምሯዊ እና ማህበራዊ ጤናን ያጎለብታል
🔹 በመጨረሻም ጤናማና ምርታማ ዜጎችን ለማፍራት ይጠቅማል፡፡
🛑 በመሆኑም የጤናማ ህፃናት ክትትል በሽታዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ከማከም ይልቅ ህፃናትን ያማከለ የጤና እንክብካቤ እንድንሸጋገር ይረዳናል።
💝 💝 #ጤናማ #ህፃናት #ክትትል መጀመር ያለበት መቼ ነው❓️
✔️ እንደተወለዱ
✔️ ከተወለዱ ከ3-5 ቀናት ውስጥ
✔️በ 1ኛ ወር
✔️በ 2ኛ ወር
✔️በ 4ኛ ወር
✔️በ6ኛ ወር
✔️በ9ኛ ወር
✔️ በ 1ኛ አመት
✔️ በ 1 አመት ከ3 ወር
✔️በ 1 አመት ከ 6 ወር
✔️በ 2ኛ አመት
✔️ በ 2 አመት ከ 6 ወር
✔️ በ3ኛ አመት
✔️ በመቀጠል በየአመቱ እስከ 18 ኛ አመታችው ድረስ የጤናማ ህፃናት ክትትል ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
💖 ለልጆዎ ጤናማ የእድገት ክትትል ለማድረግ ወይም ማንኛዉም ህፃናትን ሕክምና ሙሉ ምርመራ በህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ማድረግ ከፈለጉ በዝህ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ::
☎️ 0984650912/0939602927
💝 በቤትዎ ሆነው ስለ ጨቅላ ልጅዎ ጤንነት፣ እድገት ወይም አመጋገብ ዶ/ር ፋሲልን ለማምከር ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ ከ google play ላይ አውረደው በቀጠሮ ማማከር ይቺላሉ❗️
📞 ለበለጠ መረጃ 9394 ወይም 0964686464 ደውለው ስለ application አጠቃቀም መረዳት ይቺላሉ ::
📢 በቴሌግራም እና ፌስ ቡክ ይከታተሉን‼️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔷 ቴሌግራም : t.me/doctorfasil
🔷 FB: drfasilpediatrician
ዱክተርዬ እግዚአብሄር ይስጥልን ስለምስጠን ስለልጆቻችን የጤና ትምህርት
በጣም እናመሰግናለን D.R
Thank you
tnx daketer
Hii Dr leja 1 amet k 3 were new eyesmeles achgerna min Marg aleben
🙏🙏🙏
Thanks
❤❤❤🙏🙏🙏
5 wor 7.9
ahun 8 wor nech
ahunim 8 kilo
le 3 wor alichemerechim
ሰላም ዶክተር ስለምትሰጠን ትምህርት በጣም አመሰግናለሁ ልጄ 7 ወርዋ ነዉ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ በጣም ከሳችብኝ በጣም ጨነቀኝ ምክንያቱ ምን ይሆን?
Dr xat maxbatan indet mastaw inchlalan
Dr leje 1 amet k7 were new ena egru kiftet alew megebem enbi alegne men madreg alebegne
Doctor leja migeb magnek alechilm min madrg alebgn
ጡቴ ወትት ስለሌለው አበሸ አዘጋጂቼ እየሰጠሁት ነው ጥቅሙ ምድነዉ ጉዳቶሰ
ሰላም ዶክተርዬ ሳል ለሚያስቸግራቸው ህፃናት በቤት ውስጥ እንዴት ነው ማከም የሚቻለው??
d.R ልጀ 2አመት9ውሩ 14.4ነው ችግር አለው
እድገቱ ውይም ቁመቱ አጭር ነው መልስልኝ
ዶክተር ልጄ አምስት አመት ሆኖታል ኬሎ አስራራት ነው ምንይሻለኘል
Dr. ልጄ ራሷ ላይ ብቻ ትኩሳት አለባት / ራሷ ብቻ ይሞቃል መፍትሄው ምንድነው ?
የኔም እነደዛው እባክህ መልስ
@@hulumlebegonew3870የኔም ምንድነው
ዶ/ር በቅድሚያ ለምትሰጠን ሙያዊ መረጃ ልባዊ አክብሮቴ ካለህበት ይድረስህ 🙏
በመጠል እባክህን ለ9 ወር ህፃን ልጅ የሚሆን የምግብ ሜኑ ብትልክልኝ ።
ስለ ቶንሲል መረጃ ስጠን
Ljey 3ameta naw mgbb denant bzuh aydechm anjera mzuh aytbelam.and kilo13 nat dct shgr alebet
6 wer lay serdin segemer cemn gar new
ዶክተርዬ ልጄ 7 ወር ሆነዉ ምግብ ስሰጠዉ ቁዋቅ ይለዋል ሁለቴ ቀምሶ እንቢ ይላል ምንም ማጣፈጫ መጠቀም አልችልም አደል
lij tinsel alew yalewute sew Hager maskorte yechalale
ልጀ ላብ ያስቸግራታል ምን ልሆን ይችላል 11 ወራነው
Dr please benatik endatalfegn begeta lije sitegnam sichawetim yemankorafat aynet dimts yawetal min yishalegnal ahun 10 weru new and and sewoch yeinshirt wuta tetito new yilugnal
በ አካል ብናየው መልካም ነው ☎️ 0984650912
Adrashah yet new@@ብሩህkids
@@TigistDesale-hd5kg ☎️ 0984650912
ሰላም ልጄ1.3ወርሁናታል ኪሎዋ7.5ናትመቀን ጨርያጋጥማታል?
asa zeyt yimekeral new eske sint amet sihonu new yemijemirew d.r
ልጄ6ወሩ ነው ግን ምግብ ብዙም እሺ አይልም ጡጦም ጡትም ብዙ አይደለም መፍትሄ ካለህ
ዶክተር ልጀ ሆዱ ንፍት ያለ ነው ምን ይሻላል
ok
የኔዋ አልፋፋ አለችኝ ምን ላድርግ
8 wer nat gin betam kechin nat mefthe
ሰላም ዶክተር እባክህን የእኔ ልጅ 11 ዓመቱ ነው ማንኛውንም የሚወደውንም ሆነ የማይወደውን ምግብ ሲበላ ያስመልሰዋ ምን ተሻለኝ አልመንዳዞን ሽሮፕ 2 ገዜ አጠታሁት ግን ለውጥ የለም 🥹🙏
7 ወር ሆነው ግን ጡት ይሄን 2 ቀን ጡት ብዙአይደለም ራሱ ይሞቃል ጭዋታው ቀነሷል ??
ok