ትኩረት ለጋራ መገልገያዎች

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 30 ноя 2024

Комментарии • 6

  • @getachewwoldeyes6177
    @getachewwoldeyes6177 3 дня назад +1

    ከከተማው ማስተር ፕላን ውጭ ግንባታዎች እንዳይደረጉ ማድረግን እደግፋለሁ

  • @sina-u8o
    @sina-u8o День назад

    በኢትዮጲያ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት አለ። አለመታደል ሆኖ 90% የኢትዮጲያ ህዝብ ቅንጡ የግል መኖሪያ ቤት ገንብቶ የመኖር አቅም የሌለው ነው። የግል መኖሪያ ቤት ሲታሰብ ትልቁ ጉዳይ የመኖሪያ ቤት የመስሪያ ቦታ የማግኘቱ ጉዳይ ከቤቱም በላይ አሳሳቢና ውድ ሆኗል። በኢትዮጲያ ታሪክ የህዝቡን የመኖሪያ ቦታ ለማሟላት የመከረ ወይም የዘርፉን ችግር ለመፍታት ሥራ ነቀል ለውጣ ያደረገ መንግስት እስካሁን አልመጣም። በየትኛውም የአለም ሀገራት የመሬት ፖሊሲና አጠቃላይ የዘርፉን ችግር ለመፍታት መንግስታት የተለያዩ አካሄዶችን ቢጠቀሙም የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር በከፊል የፈቱ ሀገራት አሉ። ሀገራችን ኢትዮጲያ እንደ ሀገር የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አቅም ባይኖራትም መንግስት ይህንን ሰፊ እና ለዘመናት የተከማቸ ችግር በተወሰነ ደረጃ ለማስተንፈስ የሚወስደው እርምጃ የመንግስትን አቋምና አቅም የሚያሳይ ነው። መሬት እና የመኖሪያ ቤት ለባለስልጣን እና ለባለሃብት ብቻ የሚሆን ከሆነና መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች መሬት አግኝቶ የግል መኖሪያ ቤት ሰርቶ የመኖር ህልማቸው የህልም እንጀራ ሆኖ ከቀረ መንግስት መወቀሱ አይቀሬ ነው። በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች የመሬት አስተዳደር ና አጠቃቀም ባህላችን በእጅጉ ደካማ ከመሆን ባለፈ ህዝብ የሚኖርባቸውን የመኖሪያ ቦታዎችና ቤቶችን ከህዝቡ ፍላጎት አንፃር ከስር ከስር የመፍታት አቅማችንና ባህላችን ፈቀቅ አላለም። ይህ በሆነበት ተጨባጭ ሪል እስቴት እና የኮሊደር ልማት ተሰናስለው የሚፈጥሩት ምቹ የመኖሪያ ከባቢ ለጥቂቾች ብቻ የሚሆን ሀገር የመፍጠር ጉዞ ሆኖ ስልጣን እና ሃብት የሌለው ብዙሃኑ ህዝብ የራሱንም ቤት የመገንባት ብሎም ተከራይቶ መኖር ከአቅሙ በላይ ሲሆን የተገነባው ሀገር ውስጡ ባዶ ይሆናል። ሀገር የጋራ ቤት ናት። ድሃውም ሃብታሙም እንደ አቅሙ ተደጋግፎ የሚኖርባት የጋራ ጎጆ ናት። መሬትና የመኖሪያ ቤት ለባለስልጣንና ለባለሃብት ብቻ የሚሆን ከሆነና ብዙሃኑ ህዝብ የመኖሪያ ቤት የሚያገኝበት እድል ከጠበበ በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ሙስና፣ ሌብነት፣ ውንብድናና ስርአት አልበኝነት ይንሰራፋል። መሠረታዊ የሆነውን የመኖሪያ ቦታና ቤት ለማግኘት ሲባል የሚያስፈልገውን ብዙ ሃብት በአቋራጭ ለማካበት ሲባል ትልቁም ትንሹም የተሻለ የሚለውን አቋራጭ ለመጠቀም ይገደዳል። ይህ ተጨባጭ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ሲደመር የሚኖረው ጫና ሲታሰብ ጉዳዪ ከምንም ጉዳይ በላይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። መንግስት የሚናከናውነው የኮሊደር ልማት ተገቢ እና አስፈላጊ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለኮሊደርና ለአረንጓዴ ልማት ከተሰጠው ትኩረት በላይ መንግስት የህዝቡን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ብዙ እርምጃ መራመድ ይኖርበታል። ህዝብ የሚኖርበት ሀገር፣ ለድሃውም ለሃብታሙም፣ ለባለስልጣኑም እኩል እድልና መብት ያለባት ሀገር መገንባት የአንድ መንግስት ትልቁ ሃላፊነት ነው።

  • @adonawitsamuel
    @adonawitsamuel 2 дня назад

    ይሔ ስፍራ አያት አደባባይ ከፍ ብሎ የሚገኝ ውብ ጊቢ የራሱ የፕሮፌሰር ብርሐኑ እና የቤተሰቡ ሪል እስቴት እንደሆነ ሲነገር እሰማ ነበር። እኔም እዛው በቅርብ ርቀት ኖህ ሪል እስቴት ጊቢ ስለምኖር በዚህ አዲስ መንደር በተሰኘው ጊቢ ሁሌ እደመማለሁ። ልክ እንደ መንግስታዊው ሲ ኤም ሲ ጊቢ ውብ ነው። ግሪነሪ ነው። ሁሉ ነገር የተሟላለት።

  • @Mesfin-fu5cg
    @Mesfin-fu5cg 2 дня назад

    እብዶች

  • @onelove4538
    @onelove4538 3 дня назад

    Yete Nw Leme kura