የበዓለ ዕርገት ወረብ | Ye Beale Erget Wereb | በመሪጌታ ብርሀን ሙሴ | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 20 окт 2024
  • #እንኳን_ለጌታችን_በዓለ_ዕርገት_በሰላም_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን፤
    የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት
    ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡›› ሉቃ.24፥50 ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው›› ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በእርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡
    /ምንጭ፤ የቃል ትምህርትና በመምህር ምሥጢረ ሥሳሴ ማናየ/
    የአምላካችን ቸርነቱ ረድኤቱ አይለየን፡፡፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠

Комментарии • 7