bermel Georgis አርቲስት ካሌብ ከአዕምሮ በላይ ነው የተደረገልኝ ነገር ! | በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ታምር
HTML-код
- Опубликовано: 6 фев 2025
- ይህን ዶርቃ ሚድያ በተለያየ ነገር ለመደገፍ:-
1000115025008 ንግድ ባንክ አላዬ ወርቃገኘሁ
ዶርቃ ሚድያ subscribe share like በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
/ @dorka_media
ስልክ:-0988121212
በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ አብረውን መጓዝ ይችላሉ እና ሀሳብ አስተያየትዎን በመስጠት የተለያየ የጉዞ መረጃዎችን በመጠየቅ አብረውን መጓዝ ይችላሉ።
እኔ በርሜል ጊዮርጊስ ስጠመቅ ያየውት ልቋቋመው የማልችለው ሀይል ያለ አንደበት በአይምሮ ቃላት እንዲህ አለኝ" በሰጠሁህ እድሜ ምን መልካም ነገር ሰርተአል" ሲለኝ የምመልሰውን አጥቼ ስንቀጠቀጥ አንድ ብርሀን የለበሰ ታላቅ ሰው ከውስጥ ተርቦ እንዳበላውት ሲመሰክርልኝ ያን ሰው ለማየት ነብሴ ስትጓጓ ውልብ ብሎ ታየኝ ከዛ የሀጢያቴ ይሁን እንጃ እስራቴ ሁሉ ተፈቶ የሰው ልጅን ክብር አሳየኝ እና እየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ያለውን ፍቅር ልቤ ስር ሲገባ እንደ እሳት የሚያቃጥል ፍቅር መግለፅ የሚከብድ ፍቅር እኔ ልጆቼን ከምወድበት የሚልቅ ፍቅር
የሰው ልጅ እንዲ አይነት አምላክ እያለን በዚ ዓለም ኮተት መተብተባችን ተገረምኩ ለካ በዚ ዓለም መልካም ከሰራን ታይተን የምንሸለመው ታላቅ የክብር ቦታ አለ ለካ እውነተኛ አፍቃሪ ፍቅሩ ከምንም ነገር ጋራ የማይወዳደር አምላክ አለን
ነብሴ ወደራሴ ስትመለስ ፊለፊቴ የነበረው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስዕል አድኖ በግዝፈት ብርሃን ለብሰው ስመለከታቸው ሳለ ነበር ሙሉ ለሙሉ ወደ ራሴ ተመልሼ የነቃውት
የሚገርምነው ምን ያህል ተለወጥሸ ከዛ በአላ
ታድለህ
@@jshejsvs478እኔስ ፍራሁ ሀጣቴ በዝትዋል
ውይ መታደልህ እግዚአብሔር በቤቱ ያጽናህ 🎉
ወዮ እኔማ ምን እመልስ ይሆን በአለም አለል ዘለል ላልኩ ለኔ ወዮዉልኝ😢😢
ካሌብ አስተዋይ ሰማዕቱ እስከለተ ፍፃሜህ በቤቱ ያፅናህ
Amen ❤
እመቤቴ ኪዳነ ምሀነት አባቴ ሰምአቱ ቅዱስ ጊዎርጊስ ልድን ልፈወስ ለደጃችሁ አብቁኝና በነፍሴም በስጋዬም እረፍት ላግኝ አሜን ይደረግልኝ
አሜን ታብቃን
Amen😢
እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን የህንን የፈውሰ ቦታ የመሰረተልን እና የላክልን ክብር ምሰጋና ይግባው እኔ የምኖረው አሜሪካን አገር ነው ። እኔ በጣም ማእፀኔን ከሰባት ወር የበለጠ በፅኑ ህመም እታመም ነበር ያልወሰድኩት አንቲ ባዮቲክ የለም በመጨረሻ ሀኪሞች የወሰዱት ውሳኔ ማህፀኔ ውሰጥ ብዙ እጢወዎች ሰላሉብሸ ባጠቃላይ የውጣ ብለው እኔም ፈቃደኛ ሆኜ ተራዬን እየጠበኩኝ አንዲት እህት ልጆን ይዛ ወደበርሜል ቅዱሰ ጊዮርጊሰ ሄዳ ልጆም ተፈውሳላት አትናገርም ነበር ተፈውሳላት እና ሰትመለሰ እመነቱንና ፀበሉን ይዛ ተመለሰች ሰው ቤት ተገናኝንና ሰለሰማእቱ ፈውሰ ነግራን እያለ እኔ በፉትም ታእምራቱን እከታተል ነበር ። ከዛ እባክሸ እየተሰቃየሁ ነኝ ትንሸ ሰጪ ብያት ትንሸ ፀበልና እመነቱን ሰጠችኝ ከዛ በነጋታው ጥዋት አንድ ብርጭቆ ከመቤቴ ሰበል ጋር እመነቱን ጠብ አድርጌ ጥዋት ጠጣሁ የተረፈችኝኘ ሰውነቴ ላይ አፈሰሰኩኝ ከዛ ከቀኑ ሰባት ሰዓት እየነዳሁኝ እንደጠቅማት አጣደፈኝ መኪናዬን አቁሜ እየበረርኩኝ ወደ መፀዳጃ ቤት እሮጥኩኝ ገና በፍጥነት ቁጭ ሰል ድምፅ የለው ቢጫየተበላሸ እንቁላል የመሰል የተበጣጠሰ አሰኮል አንዴ ሸንትቤቱን ሞላው በዛን ሰዓት ፀበል የጠጣሁት ረሰቻለሁ ወይኔ ጉዴ ምንሆንኩ ደሞ ብዬ ደነገጥኩኝ የሚገርማችሁ ከዛች ሰከንድ ጀምሮ በሸታ የሚባል እጢዎቹ የተባሉት ጠፉ በድጋሜ ሄጄ ቼክ ሳደርግ የመለሱልኝ ዶክተሮቹ ሦሥት ሆነው ገቡና በጣም ደነገጥኩኝ ምንድን መድሀኒት ወሰደሸ ነበር ? ምነው ምን ተፈጠረ ሰላቸው ምንም ነገር የለብሸ ጠፍቶአል ሙሉ ጤነኛ
ነሸ ሲሉኝ እንዴት የት ጠፋ ሰላቸው አንዳንዴ ሊጠፋ ይችላል ሲሉኝ ሰማእቱ ፊቴ መጥቶ ድቀን አለበኝ ከዛ በጥብቅ የምትከታተለኝ ዶክተሬነገረኮት በአገሬ ሆሊ ወተር ጊደኛዬ አምጥታ ሰጥታኝ በዛ መድሀኔን ነገርኮት ተገርማ እሰኪ ለኒም አምጪልኝ ብላኝ አገሬ ሰሄድ የዤልሸ እመጣለሁ አልኮት እና በአእግዚአብሔር እናበሰማዕቱ ፈቃድ ትኬት ቆርጫለሁ ከገና በኃላ እመጠሸለሁ ለደጁ ከበረከቱ ለመሳለም ያብቃኝ በፀሎታችሁ አሰቡኝ አፀደ ማሪያም ነኝ አሁን ሦሰት ወር ሆነኝ ከተፈወሰኩኝ ሰማእቱ ለሁሉም ይድረሰ በያላችሁበተእ ወገኖቼ እመነት ብቻ ነው ከኛ የሚጠበቀው በርቱ ሰማእቱ ይጠብቃችሁ ይጠብቀን ። መልካም ጊዜ የሁንላችሁ። አሜን (3) ይቆየን(3)
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
❤❤❤🎉
ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን እህታችን ያሰብሽውን ያሳካልሽ አሜን እኛንም ለደጁ ያብቃን ❤❤❤❤❤❤
እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ረዳሽ ለደጁ ያብቃሽ እዛ ላሉት ላመኑት ንገሪ ባንቺ ብዙ ሰው ይመለሳል ።
አሜን አሜን አሜን ለአንቺ የደረሰ ፈጥኖ ደራሹ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ ለኔም ይድረስልኝ
እሜንሁላችንም ለደጁ ያብቃን
እናቴ አደራ ሰጥታህ ያሳደከኝ የክርስትና አባቴ የልዳው ኮከብ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈቃድህ ከሆነ ከነመላው ቤተሰቦቼ ለቤትህ አብቃን ሳትምረን ሳትፈወሰን ከቤትህ አታውጣን ከእስራታችን ፍታን የህይወታችንን እንቆቅልሽ ቋጠሯችንን ፍታልን የመዳችንን ቀን አቅርብልን በቃቹ በለን በምህረት እጅ ዳሰህ ፈውሰን ማረን ይቅርበለን❤❤❤
አቤቱ ሰማእቱ ቅዱስ ጊወሪጊስ ለደጅህ አብቃን ውድ የተዋህዶ ልጆች እኮን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደርሳችሁ ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ትኒሽ እህቴ ወደተቀደሰው ቦታ በርሚል ጊወርጊስ እደምትሄድ ቃል ገባችልይ ፍፃሜውን ያሳምርልሽ በሉይ
እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን። የ አምላክ ፍቃድ ሆኖ ሰማእቱ ደጅ ደርሼ ለመምጣት በቅቻለሁ። እና ምርት ደለጎ ኪዳነ ምህረት 5 ቀናት ቆይቻለሁ። ብቻዬን 2 ልጆች የማሳድግ ሴት ነበርኩኝ እናም እናቴ ኪዳነ ምህረትን አጋር ስጪኝ አልኳት። እና በህልሜ የታሰረ ሰው እያሳየችኝ ባልሽ እሱ ነው አለችኝ። አሁን አጋሬን ሳገኘው መናፍቅ ነበር አሁን አብረን ንሰሀ ገብተን ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሶ ልንጋባ ነው። የቅዱሳን አምላክ ምስጋና ይድረሰው። በዚህ አጋጣሚ በደረቅ ቼክ ስመለስ እንድከፍላቸው ፈቅደው ለደጁ እንድበቃ ላደረጉኝ ኤልሻዳይ ኦርቶዶክሳዊ ሚዲያ ባለቤቶች አላዬ ሰማእቱ ስራችሁን ይባርክልኝ።
ድንቅ የኦርቶዶክሳዊ ቋንቋ አገላለጥ ነው አነጋገርህ ፡ በቤቱ ያፅናህ መጨረሻህን ያሳምረው፡፡
ሰማእቱ አባቴ ድጋሜ ናፈከኝ ሳላስብህ ስላንተ ሳላወራ አልውም ስላንተ ምንም ቢነገሪ መግለፅ አይቻልም እንደ ዉሀ ትጠማኛለህ እንደ እንጀራ ትሪበኛለህ ደግሞም በጣም እፈራለሁ እየፈራህ ግን እወድሀለሁ ትናፍቀኛለህ በምንም ቆንቆ መግለፅ አይቻልም ሰማእቱ ይለያል❤❤❤
ለቤቱ ያብቃን ሰማእቱ
አሜን
Amen.
amen❤
Amen.
አሜን
አባቴ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃኝ ከነ ባለቤቴ የኔ አባት የዚህ አለም አዉሬ ሳይበላን ሰዉ አድርገን 😭😭🙏
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ እባክህ ለደጅህ አብቃኝ እባክችሁ እኔንም ውሰዱኝ
በርሜል ቅዱስ ግዮርጊስ ሄድን መንገድ ላይ ፈተና ገጥሞን ነበር ሰይጣን አንዳንደርስ ቢሞክርም አልተሳካም ሰማአቱ ደጅ ረገጥኩ የዘመናት ጥያቄ ተመለሰልኝ መልቀቅ ከምንፈልገው ሰፈር ለቀን የተሻለ ቤት ገባን በሄድኩበት ወር ለስራ ለመልቀቅ ለረጅም ጊዜ አፈልጋለሁ ግን ሳይሳካ ቀርቶ በሰማአቱ ወር ባልሞላ ጊዜ ተሳካ አቤት ድንቅ ነው
የተደረገላችሁን ኑናመስክሩ ለሰዎች ያስተምራል0988121212
Yeti new wedima
Pelese endate new megeyeho
አረ ወይኔ ደጅህ ናፍቆኛል አባቴ ድጋሚ ደጅህን ለመርገጥ ፈቃድህ ይሁን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አዎ ደጁ በጣም ይናፍቃል እኔም ናፍቆኛል
@@tigistgirma5569ታድላችሁ እኔም ለቦታው እንድሄድ በፀሎታችሁ አስቡኝ ።ወለተ ኢየሱስ
አናንተ ከኔ ትሻላላችሁ አንድም ቀን ደጁን ያላበቃንም አለ😢
ወንድም ካሌብ ከሰንበት ት/ቤት የክፍለ ሀገር ድንቅ ተልዕኮ የቅዱስ እግዚአብሔር ምሪትና በረከት የነበረው ሲሆን አሁንም ጸጋው እንደበዛልህ እናስተውላለን፡፡ሊቀ መላዕከት ቅዱስ ሚካኤል፣ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ያከበረ የቅዱሳን አምላክ ቡሩክ እግዚአብሔር ቀሪ ዘመንህን፣ ቤተሰብህንና ሥራህን አሁንም አብዝቶ ይባርክልህ፡፡
በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ ለደጅህ አብቃኝ በረከትህንና ምህረትህን ስጠኝ ደጅህ ሳልረግጥ አንተ እቤቴ ድረስ ፀበልህን አስልከህ ትንሽዬ አንገቴ ላይ እብጠት ወጥቶብኝ ከግዜ ቦሃላ በጣም እያመመኝ ነበር ፀበሉን በመስቀል ምልክት እያደረኩ ሶስት ግዜ ቀባውት ትንሽ ቆይቶ ሶስት ትንንሽ ጠጠር የሚመስል ነገር ወጣልኝ ተወኝ እግዚአብሔር ይመስገን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብር ይግባው ተሰውሬ ምንም አላየሁም በሂወቴ ላይ ያለኝ ደስታ ለውጥ በጣም ደስ ይላል ሚያዝያ ጊዮርጊስ አያቴ ትዘክር ነበር እሱ ፈቅዶ እኔ ስሙን ለማስጠራት በቅቻለሁ
ሰማእቱ አባቴ የህይወቴን አይነጥላ ጤና የነሳኝን የቡዳ መንፈስ ንቀልልኝ ፈቃድህ ከሆነ ለደጅህ አብቃኝና ልዳን😢😢😢😢😢
እህቴ ተሻለሺ
@@SeniAjanaw እግዚአብሔር ይመስገን ከሰሞኑ ትንሽ ዛሬ ደህና ነኝ የኔ ውድ❤🙏
@@ነፃነትየድንግልልጅ አይዞሺ ውዴ ፀለት አድርጌ እመቤቴ ትዳብስሺ
@@SeniAjanaw አሜን አሜን እሺ በፀሎትሽ አስቢኝ
ቃለእወትንይሳማልንእግዚአብሔርይመሲገንእእእእእእልልልልልልልል
በርሚል ቅዱስ ጊወርጊስ ሲነሳ የኔ ብቻ ነው ልብ የሚመታው ወይስ የናተም ነው ለደጁ ያብቃን 😢በስደት በናፍቆት ሞትኩኝ የሰማእቱን ደጅ አርቲስቶችን ሳይ ደግሞ ታሪኩባባ ምነው ደጁን እረቅግጦ ቢሆን ብየ ተመኘሁ😢
እኔም እደጁ የሆንኩ ያክል ይሠማኛል ❤❤❤❤😊
እግዚአቤሔር ይመስገን ክብር ለመዳህናለም ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስራው ታምር ነው አሜን 🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿አሜን🌿🌿🙏🙏🙏
አርቲስቶቻችን በርቱልን
ካሌብ ቃለ ህይዎት ያሰማልን ሰማእቱ ቅ/ጊወርጊስ ለደጅህ ያብቃኝ በረከትህ ደርሶኝ እንድመሰክር እርዳኝ አሜን።
እውነት ነው በተለይ የተዋህዶ ሰባኪ አባትና መምህር ሆነው በእነ አባ ገጽ ርማን በመተቸት የለመዱ በተሰጣቸው ፀጋ ቢያስተምሩ ይህን ቦታ ረግጠው ቢያዩት የኔም ምኞት ነው ካሌብዬ አድናቂህ ነኝ ተባረክ!!!
ቃለ ሕይወት ቃለ በረከት ያሰማህ ካሌብ ወንድማችን የእውነት መታደል ነው እኛንም በቸርነቱ ያድለን ጥሩ አገላለጽ ነው 🙏🙏🙏
በእውነት እፁብ ድንቅ ግርም ነው ሠማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስደት ምርጫ ልሰህ ለደጅህ አብቃኝ አሜን
እውነት ነው በጣም የታደልክ ንፁህ የድንግል ማርያም ልጅ ነህ ማለት ነው እንጂ፤ የዚህን ዓለም ክብርና ዝና ለሚውድድ እና እራሱን ከፍ ለሚያደርግ ሰው ይህን የተከበረ የተደነቀ የድህነት ፣ የፈውስ ቦታ ለመርገጥ ጭንቅ ነው የሚሆንበት። ክብሩ የጎደለበት ይመስለዋል። ግን ለሁሉም ሰው የ እግዚአብሄርን ድንቅ ስራ ለማየትና ለመፈወስ ያብቃን❤
በስድምት ያለነውን ልጆችህን ለንስኀ አብቃንና ለደጅህ አብቃን አባቴ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ኀፅያታችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ይማረን አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሜንን አሜንን አሜንን ❤❤❤❤❤❤❤❤
ካሌብዬ እኔ ሂሩትዬ ሁለታችሁም የሚገርም ድምፅ ነው ያላችሁ እግዚአብሔርን በዝማሬ ብታመሰግኑበት ደሞ ትለቅ ተሰፀትዎ አላችሁና ዘምሩበት እሰኪ ሰማእቱን እናመሰግነው እሰኪ አሰብበት እግዚአብሔር ይፈፀረምላችሁ። እውነት ባላለቀ የሚያሰብል ምሰክርነት ነው ቃለህይወት ያሰማልን በሀይማኖታችሁ ያፅናችሁ ፀጋውን ያብዛላችሁ ። ሰማእቱ ቅዱሰ ጊዮርጊሰ ለደጅህ አብቃኝ እኔ አሰቤያለሁ ያንተ ፈቃድ ይሁን ። ❤❤❤ አሜን አሜን አሜን 🎉🎉🎉
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃን መቸ ይሆን ሀገሬ ገብቸ ፀበል ምጠመቀው ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እርዳኝ
የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ አማላጂነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን እሜን አሜን አሜን❤❤❤❤❤❤💛💛💛💛💛💛💚💚💚💚💚🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻💐💐💐💐💐💐
እግዚአብሄር ሰላሙን ሰጥቶን ለደጁ ያብቃን። በጣም ደስ የሚል ምስክርነት ነው❤ እኔም ለመመስከር ያብቃኝ❤
ቅድስ ጊዮርጊስ ለደጅ ያብቃን ፡፡ እጀ ላይ ያበጠ ነገር ነበር ጓደኛየ የቅድስት ስላሴ እምነት ቀባችልኚ ሰርጀሪ ትሰሪያለሽ እያሉኚ ነበር ሐኪሞች ፡፡ ያለምንም ነገር ያ እብጠት የት አደገባ እፁብ ድንቅ የስላሴ ስራ ብያለሁ እግዚአብሄር ይመስገን
የቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጁ ያብቃን በረከቱ ይድረሰን
እግዚአብሔር ይመሰገን
ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን ❤❤❤
እባክህን ስማዓቱ ነፍሴን ከድቅድቁ ጨለማ አድናት ለደጅህ አብቃኝ ልጆችንም ጠብቅልኝ እባክህን ልማጸንህ ።
አሜን ❤️ አሜን ❤️ አሜን ❤️ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ለዘላለም አሜን ❤️ አሜን ❤️ አሜን ❤️ እንኳን አደረሳችሁ ለቅድስ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሰን አሜን ❤️ አሜን ❤️ አሜን ❤️ ቃል ሕይወት ያሰማልን አሜን
የሰይቱ የቅዱስ ጊዮርጊዮ ወዳቹ በፀሎታችሁ አስቡልኝ የደጁ እንዲበቃ ታመመ ወልደ ገብርኤል
እግዚአብሔር ይስጥልን በእውነት ጠያቂም ተጠያም ድንቅ ናችሁ።
እኛንም ለደጁ ያብቃን ሠማዕቱ ቅዱስ ጉዩርጊስ👏👏🌿🌿⛪🕯
እውነት እናንተ ምስክርነት ስትሰጡ የመንፈስ ቅናት ያዘኝ ለሀገሬ በቅቼ መች ይሆን ለደጅህ የሚያበቃኝ ቅዱስ ጊዬርጊስ!!!😥
አሜን አሜን አሜን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባት እባክህ ለደጂህ አብቃኝ አባት 🤲👏
Bewnt kalie yewtn yasmalen tessga berketn yestlen wendmaechntebarik fetary ysetlen❤❤
ወንድማችን እንኳን ለቤቱ በረከት አደረሰህ
እውነት ነው እንቁ አባታችን መላከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙም አንተም ከገልፅከው በበለጠ ስለ የኔታ ትምህርት ቤት ምን ያህል የእግዚአብሔር ጸጋ ጥበብና የሞገስ ምን ያህል የእግዚአብሔር ፍቅር እርስ በርስ መዋደድ እና መከባበር እንደነበረው ያስረዳሉ ወንድሜ ለአሁኑ ማንነትህ ያ ሁላ የተባረከ የመንፈስ ቅዱስ በረከታዊ መሰረት እንዳለውም ያስረዳሉ በርሜል ጊዮርጊስ አሁን ያለበት ሁናታ በጣም ሊገርመን ይችላል ግን የሸንኮራ ዬሀንስን የድሮ ሁኔታም እንደዛ ነበር እግዚአብሔር ለሁሉም ምክንያት አለው
❤❤❤🎉
ካሌብዬ እንኳን ሰማእቱ እረዳህ!!ለሁላችንም መድሀኒአለም ይፍቀድልን ለደጁ ያብቃን
አሜን አሜን አሜን ቅዱስ ጌወጊስ ለደጂክ አብቃኝ አባቴ ❤
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ እርዳኝ አግዘኝ ለደጂህ አብቃኝ የዘላለም ምኞቴ ነው. አቤት መታደል ከዚህ በላይ ምን መመረጥ መጠራት አለና
አሜን♥️ አሜን♥️ አሜን♥️
ቅድስት ብሩክታዊትን ከሰይጣን ወጥመድ የጠበካት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ ሆይ አንቴን ጠይቀ ያጣሁት ነገር የለምና ዛሬም እንደ ልጅነቴ በንፁህ አንደበቴ አመሰግንህ ዘንድ እርዳኝ ከፈጣሪዬም አስታርቀኝ። በመንገዴ ሁሉ ከክፉ ጠብቀኝ።♥️🙏♥️🙏♥️
አቤቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ለደጅህ አብቃን እንደ ሀጢአታችን ሳይሆን እንደ ምህረት ህ😢😢😢😢😢
ሰላምህ ይብዛ ካሌብ ወንድሜ እግዚያብሔር አብዝቶ ይባርክህ እንወድሀለን❤️
ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ ምግባር ከኔ ምንም የለ እባክህ ሰባት አመት በተጋደልክለት አምላክህ ብለህ ተለመነኝ እዚሁ ባለሁበት ታምርክን ግለፅልኝ የጎደለኝን ታዉቃለህ😢😢😢
😢😢😢
አቤቱ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃኝ
እግዚአብሔር ይመስገን ህይወቴን ስበጠብጠው የነበረው ምስጥር ተጋለጠ እንዲሁም ሌሎች ተጋልጠዋሎ ።ይህ ሁሉ ተአምር በ7ቀን ቆይታ ነበር ።በርሜል ቅዱስ ጊዬርጊስ አሁንም የጀመርከውን ጨርስልኝ አሜን
በምን ላግኝሽ information ፈልጌ ነው
በቤቱ ያፅናህ እኛንም ለደጁ ያብቃን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ሰማዕቱ ፍቃድህ ይሁንልኝና ለደጅህ አብቃኝ
ጊዮርጊስ ሆይ እባክህ እኔንም ደጅህን አሳይተይ ለመመስከር አብቃኝ
አባቴ ደጅህን ሳረግጥ በድንቅ ፀበልህ ሳልዳሰስ አልሙት ❤❤❤❤❤❤❤
ቅዱስ ጊወርጊስ ያሳደግህኝ መላክ ቤተሰቦቼን ጠብቅልኝ ለሀገሬ በሰላም አብቅተህኝ ደጂህን እድረግጥ እርዳኝ አባቴ በደጅህ አሳድገህኛል አተ ምን ዬሳንሀል ሁሉን ታደርግልኛለህ አባቴ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏🙏
እግዚአብሔር ይመስገን ለደጅህ አብቃኝ ሰማዕቱ አባቴ ❤❤❤
.ሠመአቱ ቅዱስ ጊወርጊስ ለዚህ ቅዱስ ስፍራ አብቃን ይብቃን ስደት እርዳን ሠመአቱ
ቃለህወትን ያሰማልን የሰማእቱ በረከት ይደርበን እናም እደዚህ አይነት የተቀደሰ ቦታ ስንሄድ ምናለበት በረከትን ቢሰራ ምክንያቱም አኪቤት ብንሄድ ስትናስት ብርነው የምናፈሰው ግን እደዚህ አይነት የተቀደሰ ቦታ ስንሄድ ምንም ሳንይዝ አይከብድም አካባቢውንም መንገዱም ባተክርስትያንንም መስራት መልካምነው እኛ የስን ቤትስንሰራ ሰማአቱና ቆራ ቅድስት ኪዳነምህረት የኛንቤት ይሰሩልናል
Betam des yemik agelalelets new. Thank you.
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኛ አባት ከእቅፍህ አታዉጣን 🤲🤲 ለደጂህ አብቃን 😔
Qale heywet yasemalen bedeme betena tebeqo yanurelen Ehete Egziabeher kenelejochesh Cheru Egziabeher tebeqo yanuresh melekam sew nesh. Teyqiwm Tebarek Semat Bermaeil Giyorgis lehulschem dereselen Amen.
Semayatu qidus goriges ledeju yabeqagn🙏🙏🙏
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
- ዮሐንስ 3፥16
ሰማአቱ ቅዱስ ጊወርጊስ ሆይ ለደጅህ አብቃኝ🤲🤲🤲
ልደጂ ያብቃን ቅዱሰ ጊዮርጊሰ❤❤🎉
ተዐም ነው የዐምላክ ስራ አይተወንም ሰዐመአቱን ልኰ ይህን ሁሉ ተኣምራት ይሰራል ተመስገን እኛንም ለቦታው ለደጁ ያድርስን አሜን
Lebitu yabikan kidus gworgis abati ,,🙏🙏
አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተነሳብን የጠላት ዳቢሎስ ቁጣ ይታደገን
አሜን ፫ ይሁንልን ይደረግልን ፣ መታደል ነው
አቤቱ ሰማኢቱ ቅዱስግዮርግስ ለቤትህ አብቃኝ።
የሚገርም ነው አርቲስት ገኒ youtube ላይ ሲመሰክር አይቼው ነበር ❤
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እባክህ ለደጅህ አብቃኝ
ድህንነት እፈልጋለሁ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈውስ እፈልጋለሁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃኝ
ባለሁበት ቦታም ፈውስኝ አባቴ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቴ ለምስክርነት አብቃኝ የሄዳቹ ታድላቹ ለኛም ፀልዩልን
የቋራው ሰማእቱ ቁዱስ ጊዬርጊስ በእ/ር ፍቃድ ካለንበት ውስብስብ ችግር እና መከራ ተጠርተን የፈውሱ ተቋዳሽ እንድንሆን ያድለን አሜን
ሰማእቱ ቅዱስ ጊወርጊስ አባቴ ለደጅህ አብቃን
እንኳን ደህና መጣህ
እግዚአብሔር አምላክ ለደጁ ያብቃን ሰማአቱ ሁላችን ይጥራን እኔጨንቆኛል እስከምህዳ😢😢😢
ሰማአቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ ለደጅህ አብቃኝ
የሰማእቱን ደጅ የረገጣችሁ ታድላችሁ እኚንም ለደጅ ያብቃን ሀገራችንን ሰላም ያድርግል❤❤❤
ሰማቱ ለተቀደሰዉ ቦታያብቃን❤❤❤
ሰማህቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃኝ ❤❤❤❤❤❤❤❤
ሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደጅህ አብቃኝ እኔም ድንቅ ስራህን የምመሰክር አድርገኝ
ኣሜን❤❤❤ኣሜን❤❤❤ኣሜን❤❤❤❤❤❤❤
ሰማአቱ ቅዱስ ጊዎርጊስ ለደጅህ አብቃኝ
ለደጁ ያብቃን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ🙏
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜን ❤️🙏🙏🙏
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮረግስ ለደጅህ አብቃኝ 😢
ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊሰ እኔንም ለደጅህ አበቃኝ ከነ ልጆቼ በረከትህ ይድረሰን 💚💚💚💚💚💚💚
አቤቱ ሰማእቱ ቅድስ ጊዎርግስ ይቅር ይበሉኝ 🤲🤲🤲😭😭😭
ሰማኣቱየ የልቤ ኣንተ ታውቃለህ ና የልቤ ምሽት ፈፅመልኝ ❤❤❤
እናተ ሰትመሰክሩ እባዪን መቆጣጠር አቃተኝ ግን እኔ ሁለቴ ሄጃለሁ አስጓዦች በሚዲያ ምመኑን ይቅርታ ይጠይቁ እዴት እዳሰቃዪን እነሱና እኛ እንተዋወቃለን ፈረሰኛዉ ቅዱስ ጊወርጊስ ሁላችንንም ይቅር ይበለን እዉነቴን ነዉ ገዘብ ያለቀበት ሰዉ እሚበላዉ አቶ ሲለምን አይቻለሁ ጎደር ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰፍረን እና አላዪ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቁ ብዙ ሰዉ ተቀይሟል
ማለት ግልጽ ብታደርጊው የተፈጠረውን ነገር?
እውነት ነው ድልድይ ቢሰራ ክረምትም እንድንጠመቅ ይረዳል
በእውነት የኤኔታ ትምህርት መቅረት አልነበረበትም አሁን መሰልጠን ብለው መሰይጠን ውስጥ ተገባ
ዛሬ አባየይ ቅዱስ ሚካኤል ናፍቆኝ ስዕል አድህኖ አይቼ ነው የገባሁት ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮሪግስ እኛም ከስደት መልስ አብቃን🎉
ጎበዝ በ እዉነት አገላለፅህ የገባህ ንቁ ክርስቲያን ነህ። በተለይ በምቾት ዉስጥ ዋጋ አታገኙም ያልከዉ 👍
እግዚአብሒር ይመሥገን ለናንተ የደርሰ ሊቀ ሰማእት ቆድሰ ጊወርጊሰ ለኛም ደርሱልን ለደጅ ያብቃን
አምላከ ጊዮርጊስ እግዚአብሔር ይመስገን❤❤❤
Amen Amen 🎉🎉🎉🎉❤❤❤
አቤት በተሰጠ ፀጋ የሰማዕቱን ደጅ ስትገልፀው እኔ ራሱ አብሬ ሄድኩኝ አምላኬ ሆይ እንደበደሌ ሳይሆን እንዳንተ ቸርነት በድንግል ማርያም አማላጅነት ቦታውን እንድረግጥ ፍቀድልኝ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ አንተው እርዳኝ
ሰማቱ አባቴ ከነቤተሰቦቼ ከታሰርንበት እስራት ፍታን. 😢ለደጅህ አብቃኝ አባቴ ከበርከቱ ሳልካፍል እዳልሞት