Размер видео: 1280 X 720853 X 480640 X 360
Показать панель управления
Автовоспроизведение
Автоповтор
ለመጀመርያ ግዜ የሰማውትም ሸገር ላይ ነው። በሰማውት በወሩ በዘፈን ተለቀቀ። የትልቅ ሰው ስራ በትልልቆቹ ሲቀርብ ይረዱታል። ጋሽ ገ/ክርስቶስ ደታ። ውዴ ስወድሽ!!
እኔ እወድሻለሁ/ገብረክርስቶስ ደስታ /ብዙ ሺህ ዘመናትእልፍ አእላፍ ሌሊትሚሊዮን መሰለኝፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ።እኔ እወድሻለሁየሰማይ መሬቱንየባህር ስፋቱንየዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህልእንደ ፅጌ-ረዳእንደ አደይ አበባእንደ ሎሚ ሽታ፡፡እንደ እጣን ጢስ እንጨት፣ እንደ ከርቤ ብርጉድ፣እኔ እወድሻለሁ፣አበባ እንዳየ ንብ፡፡እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰውፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰውማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋርአማርኛ አይበቃ፤ወይ ጉድ!ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፣እኔ እወድሻለሁእንደማታ ጀንበር።እንደ ጨረቃ ጌጥ፣ እንደ ንጋት ኮከብ፣እኔ እማልጠግብሽስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፡፡ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረውጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው።ጣይ እንዳየ ቅቤገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፣አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው፣ፍቅሬ አንቺን ስወድሽብዙ ሺህ ዘመናትእልፍ አእላፍ ሌሊትውድ እወድሻለሁ፣ዐይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁስወድሽ ስወድሽእኔ እወድሻለሁ።16/9/1960ዓ.ም የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ/ገብረክርስቶስ ደስታ/
ለመጀመርያ ግዜ የሰማውትም ሸገር ላይ ነው። በሰማውት በወሩ በዘፈን ተለቀቀ። የትልቅ ሰው ስራ በትልልቆቹ ሲቀርብ ይረዱታል። ጋሽ ገ/ክርስቶስ ደታ። ውዴ ስወድሽ!!
እኔ እወድሻለሁ
/ገብረክርስቶስ ደስታ /
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ።
እኔ እወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌ-ረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደ ሎሚ ሽታ፡፡
እንደ እጣን ጢስ እንጨት፣ እንደ ከርቤ ብርጉድ፣
እኔ እወድሻለሁ፣
አበባ እንዳየ ንብ፡፡
እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር
አማርኛ አይበቃ፤
ወይ ጉድ!
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፣
እኔ እወድሻለሁ
እንደማታ ጀንበር።
እንደ ጨረቃ ጌጥ፣ እንደ ንጋት ኮከብ፣
እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፡፡
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው።
ጣይ እንዳየ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፣
አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው፣
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ውድ እወድሻለሁ፣
ዐይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ
እኔ እወድሻለሁ።
16/9/1960ዓ.ም የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ
/ገብረክርስቶስ ደስታ/