አቡቀለምሲስ - የዮሐንስ ራዕይ- Apocalypse 022 - 13:1-10 ... 144 ሺሆቹ
HTML-код
- Опубликовано: 28 янв 2025
- ራዕይ 14፡1-10
ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።
2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።
3 ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥
4 ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
5 አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
6 ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።
7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥
8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።
9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል። አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
11 እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
12 ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
15 እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
16 ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።
17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤ [18] በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።
በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።
2 ብርቱም መልአክ። መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
3 በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።
4 መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።
5 ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።
6 በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከልም በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ፥ ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።
7 መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።
8 መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።
9 -10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
11 አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥
12 በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።
13 በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ።
14 አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
አሜን አሜን የኔ አባት እግዚአብሔር ይባርክ ኖርልን የኛ በረከት ምን ይባላል አተን የሰጠን ጌታ ይባረክ❤❤❤❤❤❤
አሜን ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን ፓስተርዬ ተባረክ ዘመንህ አገልግሎትህ ኖሮህ ጤናህ ሁሉ በጌታ እየሱስ ስም የተባረከ ይሁን መንፈስ ቅዱስ ፀጋውን ያብዛልህ
ዙም እዴት እደሚገባ አላቅም ውቀት የለኝም ስላተማርኩ ማንበብ አልችልም ግን በይቱብ ከተለቀቀ እደዚህ ሰማለው ፀልያለው 3አመት አመት በፆም ተካፍያለው ፆማለው እድል እኮ ነው❤
እውነት እኔም ቡዙ አላነቡ መግባት እፍልግ ነበር ግን አልቻልኩ እኔድ ምንም ብየ ነው አማርኛ ምፀፉ
Pastor geta yebarkhe❤❤❤❤❤❤😊
አሜን ❤❤❤❤❤❤❤
Amen Amen❤❤❤❤❤❤
ፓስተር ተባረክ ፀጋ ይብዛልህ!
God blessed you pastor ✝️🙏🏽
ፓሰተርዬ ጌታ ይባርክህ !!!
አሜን
ጌታ,እየሱሱስ,ክርስቶስ,አብዝቶ,ይባርክህ,ክብሩ,ሁሉ,ጌታ,ይውሰድ
ጌታ ሆይ ቶሎ ናለን ማራ. ናታ አሜንንን ፓስተር ጌታ አብዝቶ ይባረክ ❤❤❤❤❤❤❤
በጣም የሚጣፍጥ ገበታ ነው የሚያቀርቡልን የረዳዎት ጌታ ስሙ ይባረክ እርሶም ብርክ በሉ ፈርቼ ያስቀመጥኩት አይገባኝም ብዬ የተወሰደው ኩትን በእርሶ ምክንያት አፒታይቴ ተከፈተ ፍርሀቴም ተወገደ እና ተባረኩ
ይሰማል ፓስተር
ፓስተር የጌታ ጸጋ አሁንም አብዝቶ ይባርክህ ጉልበት ይሁንህ
እግዚአብሔር ይባርኮት እዉነተኞዉነ ወንጌል እነፀልያለን እዉነተኞ ወንጌል እንዳይነገር ተግዳሮት የሜመጣ ሰራዉ ይፋረሰ በርታ ፐሰተር ✝️🙏
ፓስተር ጌታ ፀጋውን ያብዛልህ ጉልበት ይሁንልህ
🎉🎉🎉
Amen God bless pastor🙏
አሜን ሀሌሉያ
geta yibarkih pasteriye
መምህር እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ!!
እባክህን ለወንድሜ ጸልይለት በጣም ችግር ውስጥ ነው ያለው
😢 መተት ተደርጎበታል
እባክህን መምህር
Please Pastor Assefa የቤተክርስቲያን ታሪክ milew video playlist alikeftim alegn mn yishalegnal ebakih begeta tebaberegn
ሰላም ፓር አስፋው ከዚህ በፊት መንበረ ጸባኦት በሚል ርእስ ያስተላለፍከውን ትምህርት አይቸው ሳልጨርስ ተቋረጠብኝና ደግሜ ለመስማት ብፈልግ አጣሁት እባክህ እንደገና ብታቀርበው? አመሰግናለሁ ተባረክ።
አልተቆራረጠም
ፓስተር ጌታ ፀጋውን ያብዛልህ ጉልበት ይሁንልህ