የሚንተከተክ ውሃ፣ የሚጋረፍ እንፋሎት፣ የሚሰነፍጥ ሽታ - በመሬት መንቀጥቀጥ የፈለቁ የአፋር ፍልውሃዎች ሁኔታ | Ethiopia | Afar | earthquake

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 6 фев 2025
  • ባለፉት ሳምንታት በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ ተከስቷል። በዛሬው ዕለት ንጋት ላይ የደረሰውን ጨምሮ፤ በክልሉ ባለፉት ቀናት የተለያየ መጠን ያላቸው ርዕደ መሬቶች ተመዝግበዋል።
    በፈንታሌ እና ዶፈን ተራራዎች መካከል ባሉ ስፍራዎች በደረሱ የመሬት መንቀጥቀጦች፤ ከፍተኛ ግፊት ያላቸውን ፍልውሃዎች በተለያዩ ቦታዎች እንዲፈልቁ አድርገዋል። ክስተቱ በብዛት ወደታየበት ወደ ሳገንቶ ቀበሌ በቅርቡ ተጉዞ የነበረው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፤ አንዳንዶቹ ፍልውሃዎች የፈለቁት በሰዎች መኖሪያ አቅራቢያ መሆኑን ተመልክቷል።
    በእነዚህ ስፍራዎች የሚገኙ የእርሻ ቦታዎች፤ ጭቃ በተቀላቀለበት ውሃ ተሸፍነዋል። ከመሬት ተስፈንጥሮ የሚወጣው የፈላ ውሃ፤ በአካባቢው ያሉ ዛፎችን እና ሜዳዎችን ጭምር ጭቃ አልብሷቸዋል። ከፍልውሃዎቹ ዙሪያ ያለው ቦታም፤ በረግረጋማ ደለል የተሞላ ነው።
    በተለያዩ አካባቢዎች የፈለቁት ፍልውሃዎች፤ ከፍተኛ ሙቀት ያላቸው እንፋሎቶችንም አብረው ያመነጫሉ። የሚጋረፈው እንፋሎት ተቋቋሞ ወደ ፍልሃዎቹ የሚጠጋ ሰው፤ የሚሰነፍጥ ጠረን ያውደዋል።
    እንዲህ አይነት ክስተቶችን ከዚህ ቀደም ተመልክተው እንደማያውቁ የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፤ በሆነው ነገር ሁሉ ከጎብኚዎች እኩል ሲደመሙ ይታያሉ። የነዋሪዎችን እና የአካባቢውን ሁኔታ፤ ከቪዲዮው ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
    ---------------------------------------------------------------------------------------
    የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦
    ድረ ገጽ ፦ ethiopiainsider...​
    ፌስቡክ ፦ / ethiopiainsider
    ትዊተር (ኤክስ) ፦ / ethiopiainsider
    ቴሌግራም፦ t.me/EthiopiaI...
    ቲክቶክ፦ / ethiopiainsider

Комментарии • 19