የመንግስቱ ፕሮቶኮል 2016 ክፍል 1
HTML-код
- Опубликовано: 26 ноя 2024
- ኪዳን እና ታማኝነት
📌አምላካችን የኪዳን አምላክ ነው!
🤝ኪዳን እግዚአብሔርን ከሰው፤ እንዲሁም ሰውን ከሰው የሚያስተሳስር ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል እና የበረከት ምስጢር ነው። ኪዳን እጅግ አስደናቂ መንፈሳዊ ምስጢር ነው
ምስጢር ማለት ከላይ ያለ እና በቀላሉ የምናየው ስላልሆነ ቶሎ ተጠቃሚዎች እንዳንሆን ሊያደርገን ይችላል አጥብቆ የፈለገው ግን ይደርስንበታል፤ የከበረ ነገር የሚገኘው አጥልቀህ በቆፈርክ መጠን ነው! የኪዳንን ምስጢር ለመረዳትም የእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ነው የሚረዳን!
📌ኪዳን የግንኙነት መሰረት ነው! ኪዳን አልባ ግንኙነት፤ እንደ መሰረት አልባ ቤት ነው
መንግስታት የሚጸኑት በኪዳን ነው! ቤተሰብ የሚጸናው በኪዳን ነው! ቤተክርስቲያን የጸናችው በኪዳን ነው!
🤷ኪዳን እና ውል ሁሉ ቦታ አለ፤ ሰው ግን አያስተውለውም
ኪዳን አልባ ግንኙነት ሁሉ መካን ግንኙነት ነው!
🔑ኪዳን የእግዚአብሔር ቢሮ ነው! እግዚአብሔር እንዲሰራ ስትፈልግ የምትሄደው ወደ ኪዳን ነው! እግዚአብሔር ከኪዳን ውጪ ምንም ነገር ሰርቶ አያውቅም!
እግዚአብሔር የኪዳን አምላክ መሆኑን ማወቅ በህይወት እረፍትን ይሰጣል:: እግዚአብሔር እራሱን በኪዳን ማሰሩ ለሰው ልጆች ጥቅም ሲል ነው!
ኪዳን ምንድነው?
ኪዳን በሁለት አካላት መካከል ለጋራ ጥቅም የሚደረግ በፍርድ የሚጸና ውል ነው።
*በሁለት አካላት መካከል ለጋራ ጥቅም የሚደረግ
🙋♂️ለብቻ መሆን ምን ችግር አለው? የሁለት አካላት አብረው መሆን ለምን አስፈለገ?
“ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ 'ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ' አለ።”
📖ዘፍ 2፡11
📌እግዚአብሔር "የፈጠርኩት ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" አለ! ስለዚህ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የተባለው እንዴት እና ለምን ሰውን እንዳበጀው የሚያውቀው ፈጣሪው ነው! ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አለመሆኑን ማመን ለግንኙነት የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ያደርግሃል!
ስለዚህ ሰው በህብረት ወይም በግንኙነት ውስጥ መሆኑ መልካም ነው! (መክብብ 4፡7-12) ግንኙነት ወይም ህብረት እግዚአብሔር በረከቱን፣ ሕይወትንም እስከ ዘላለም ያዘዘበት ስፍራ ነው 👉መዝሙር 133
📌ብዙ ሰው በግንኙነት ውስጥ ያለውን ግጭትም ሆነ ተያያዥ ነገሮች ፍራቻ ግንኙነትን ይሸሻል የህልውና ጉዳይ መሆኑን የተረዳ ግን ነገሩን በጥበብ ለመያዝ ጥበብን ይፈልጋል
📍በህብረት ኢየሱስ በህያውነት ሊስራ ይገለጣል! "ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።” ማቴዎስ 18:20
🤝ሕብረት በረከት ነው! ብቻ መሆን እርግማን ነው!
📌ኪዳን በሁለቱ አካላት መካከል የሚገባ የግንኙነት ፕሮቶኮል ነው
የመንግስቱ ፕሮቶኮሎች የበረከት እና የሕይወት ደጆች ናቸው! የዓለም ፕሮቶኮሎች የእርግማን እና የሞት ደጆች ናቸው!
*ሁለቱ አካላት ግንኙነታቸው ከሁለቱ በአንዱ አቅጣጫ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል። ወደ ላይ እና ወደ ታች ወይም ወደ ጎን
ወደ ላይ እና ወደ ታች ያሉ ግንኙነቶች የመወራረስ ጥቅም ሲሆን ያላቸው ወደ ጎን ያሉ ግንኙነቶች የመረዳዳት ጥቅም ነው ያላቸው
አንድ ሰው ሁለቱም የግንኙነት አይነቶች በህይወቱ ሲኖሩ ብቻ ነው በበረከት ህይወት መኖር የሚችለው!
Amen 🙏
Covenant and loyalty What an enlightenment. It is an eye opening. Apostel you are our blessing!
Thank you so much Sir!
Life changing truth! Covenant and Loyalty
❤❤❤AMEN
Wowww 🥰 👌 🥰 🎉
Wawu God Bless you