የአዲስ ዓመት መልዕክት "መዞር ይበቃችኋል!"
HTML-код
- Опубликовано: 13 сен 2024
- ይህ ቪዲዮ የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት (2014 ዓ.ም) በማስመልከት ወንጌላዊ ያሬድ ያስተላለፈው አገራዊ መልዕክት ነው። የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ በኋላ ከኤርትራ ባሕር እስከ ከነዓን ለመድረስ የፈጀባቸው ብዙዎቻችን እንደምናስበው 40 ዓመት ሳይሆን 2 ዓመት ብቻ ነበር። በሁለት ዓመት የተስፋይቱ ምድር በር የነበረው ቃዴስ በርኔ ከደረሱ በኋላ እግዚአብሔርን ባለማመናቸው ምክንያት እግዚአብሔር በቁጣው ማለባቸው። መሐላውም ከእነዚህ ከናቁኝ አንድስ እንኳን አያይዋትም በሚል ነበር። ስለዚህ ይህ የማያምን ትውልድ ሞቶ እስኪያልቅ የእስራኤል ልጆች የሴይርን ቅጥልጥል ተራሮች ለ32 ዓመታት መዞር ነበረባቸው። አንድን ስፍራ ለ32 ዓመታት መዞር አድካሚ፣ አሰልቺ፣ አታካች ጉዞ ነው። ያ የማያምን ጠማማ ትውልድ ሞቶ ሲያልቅ እና አዲስ "የኢያሱ ትውልድ" ሲነሳ እግዚአብሔር "አሁን ይህንን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር ውጡ አለ።
የኢትዮጵያም ሁኔታ እንዲሁ ነው። በ1960ዎቹ የተነሳው የመማርና የመሰልጠን ዕድል ያገኘው ትውልድ ታበየ፣ እግዚአብሔርን ናቀ፣ "አምላክ የሚባል የለም!" አለ። ከዚያም በየዩኒቨርስቲዎቹ በባዕድ ፍልስፍና ተሞልቶ ሕ.ወ.ሃ.ት፣ ኢ.ህ.አ.ፓ፣ ኦ.ነ.ግ፣ ፣ ወታደራዊ ደርግ፣ ሜ.ኤ.ሶ.ን፣ ወዝሊግ፣ ኢ.ጫ.ት፣ ኢ.ማ.ዴ.ሊ … ወ.ዘ.ተ በሚል ተደራጅተው 47 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን የማትወጣበት አዙሪት ውስጥ ከተዋታል።
ኢትዮጵያ የተስፋ አገር ናት! ተስፋዋም እውነተኛ አንድነት ነው። አንድነት ልዩነትን የማይረግጥበት፣ ልዩነትም አንድነትን የማይውጥበት የመከባበርና በጋራ የመኖር እሴት ርስቷ ነው። ተስፋዋ፣ እውነተኛ ፍትሕ ነው። የሕግ የበላይነት የሰፈነበት፣ ብዙሃኑን የሚሰማ፣ ለትናንሾችንና ለደካሞች የሚፈርድ ፍትሕ ርስቷ ነው። ተስፋዋ፣ በተለወጠ አስተሳሰብ፣ በታደሰ አእምሮ በመልካም የሥራ ፈጠራ ባሕል፣ የትጋት ባሕል፣ የጊዜ አጠቃቀም ባሕል፣ የንባብና የምርምር ባሕል፣ የተግባቦት ባሕል ርስቷ ነው። በእነዚህ ርስቶች አጠገብ ናት፣ ነገር ግን መግባትና መውረስ አልቻለችም።
እነዚህን ምድራዊ ተስፋዎቿን ለመውረስ ግን አንድ ነገር መሆን አለበት። የቀደሙት የ60ዎቹ የክህደት ትውልድ እርሾ ከዚህ ትውልድ ወጥቶ ማለቅ አለበት። ያ የክፋት፣ የተንኮል፣ የሴረኝነት፣ የጦረኝነት፣ የዘራፊነት፣ የዘረኝነትና የመለያየት እርሾ ዛሬም የመውደቅና የመውደምን ተራሮች እንድንዞር ዳርጎናል። ያ እርሾ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ኢትዮጵያ ሥልጣን በጠመንጃ አፈ-ሙዝ የሚያዝባት፣ በጉልበት ያሸነፈ የወደደውን ሕግ የሚጭንባት፣ ሁሌ እንደ አዲስ የምትመሠረት ኋላ ቀር አገር ከመሆን አትወጣም። የአንድነት፣ የፍትሕና የዕድገት ተስፋዋን አትወርስም።
ይህ ትውልድ ፈጥኖ መንቃት አለበት። የቀደሙቱ አስተሳስብ በዚህ ትውልድ ውስጥ መሞት፣ መጥፋትና መክሰም አለበት። በምድረ በዳሊሞት የሚገባውን በእግዚአብሔር የተጠላ አስተሳሰብ አንግቦ የሚሰዋና የሚሞት ትውልድ መኖር የለበትም። ትውልዱ ወደ ኋላ ዘር እየቆጠረ፣ የ60ዎቹን ትርክት እየቀመረ መሠዋት የለበትም። ይልቅ ያንን ድሪቶ ከላዩ አሽቀንጥሮ ጥሎ ተስፋውን ለመውረስ በእምነት መገስገስ አለበት።
ያኔ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማማ፣ የምድር ጌጥ ትሆናለች። ያላት የተፈጥሮ ጸጋ ይገለጣል። ሕዝቧ በነጻነት ተዋዶና ተከባብሮ ይኖራል። ሕጻናት በደስታ የሚቦርቁባት፣ የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምጽ የሚያስተጋባባት፣ አዛውንትና አረጋውያን ዕድሜ ጠግበው፣ ጥሪታቸውን ለልጆቻቸው አውርሰው፣ ትውልዳቸውን መርቀው፣ በልጅ፣ ልጆቻቸው ተከበው የሚያሽልቡባት ምድር ትሆናለች። መዞር ይብቃን! በቃችሁ ይበለን! አዎን እግዚአብሔር በቃችሁ እያለን ነው። እኛም የ60ዎቹን የክህደት ትውልድ አስተሳሰብ አውልቀን እንጣል።
መልካም አዲስ ዓመት
2014 ዓ.ም
አሜን እሜን !!!!!!
ወንጌላዊ ያሬድ እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ 🙏🏻
አሜን አሜን አሜን 🙏እግዛብሔር ዘመንህን ይባረክ ይሆናል ደርሷል እድሜ
ይስጠን እናያለን ጌታችን ታማኝ ነው
በእውነት መጠበቅ ብቻ ነው።
ብዙ ነብያቶች ከተነበዩት ትንቢት የተለየ በእውነት ላይ የተመሰረተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምድራችን የተላከ መልእክት ነው ጌታ ይባርክህ ወንድሜ ያሬድ
በዚህ በጨለማ ዘመን ተስፋ ስለአሳየሀን ጌታ ከዚህም ጨምሮ ፀጋ ያብዛልህ ወንድሜ ያሬድ! ጌታን የበለጠ እንዳውቀው እና ወደ ጌታ የበለጠ እንድቀርብ ረድተህኛል! ጌታ ያብዛልህ! ትምህርቶችህን ማስታወሻ ይዤ ነው የምቀጣጠለው! በልበ ሙሉነት የእሱን ትምህርት ተቀጣጠሉ ማለት ከምችላቸው ጥቂት ሰዎች የመጀመሪያው አንተ ነህ! ለአንተ እና ለቤተሰብህ መልካም አዲስ አመት!
አውነትም ዙረት አውነትም ድግግሞሽ የሚያሰለች የሚያሳዝን አንድ አይነት ስንሰማና ስናይ የኖርነው አሰቃቂ ነገር ብቻ ጌታ ሆይ እኛንም እንደ እስራኤላውያን በቃችሁ በለን።
እስራኤላው አይደለንም ያለ አለ? እነዚህ ፈረንጆቹ ምድራችን ላይ ተቀምጠው እስራኤል ነን ይላሉ...
አብዛኛው የሰሜን ሕዝብ በተለይም የትግራይ ህዝብ original እስራኤላውያን ናቸው:: የእውነት እስራኤላውያን እንደኛ ሜሊነን ወይም የስውነታችን
የቀለም ኢንዛይም ነው:: ክርስቶስ ራሱ ጥቁር እንደሆነ ይናገራል
ያሬድ አንተና ቤተሰቦች በዚህ ዘመን እግዚአብሔርን በእውነት ለሚፈልጉት ሰዎች እንዲያገኙትና እንዲያውቁት የተሰጠኽን ስጦታችን ነህ ጌታ ዘመንህን ይባርክ!!!
ጌታ እየሱስ ይባርክህ ...እግዚአብሔር በቃቹ ይበለን
የ66ቶቹ ትውለደ ኢትዮጵያውያን ጌታን በሚያመልኩ በሚያገለግሉ ተተኩ። ሀሌሉያ ሀሌሉያ ሀሌሉያ
ያሬዶ እንኳን አብሮ አደረሰን፡፡ ሁል ጊዜ ሳስብ በዚህ ዘመን አንተን የሰጠንን ጌታ አመሰግናለዉ፡፡ ላለፉት አመታት በ ኦንላይን የምታስተላልፋቸዉ ከኤፌሲዮን፣ ሮሜ ፤ ዮሴፍ፤ ዕብራዊያን እና የተለያ ትምህርቶችህ ለመንፈሳዊ እድገቴ ጠቀሙኝ ከምላቸዉ ነዉ፡፡ በሚመጣዉ አመት አንተም ምታብብበት አመት ይሁን ለቤተሰቦህ ሁሉ መልካም በዓል ይሁን፡፡ በጣም እወድሐለዉ፡፡
ተባረክ ያሬዴ! ትምህርትህ ሁሌም ይባርከኛል! የሚጣል ቃል የለውም. ተባረክ!
አንተ ከጌታ የተሰጠህን ውዱ ስጦታችን ነህ ከ ጌታ የተሰጠህንም መልካም አደራ በአግባቡ እየተወጣህ እና እውነተኛውን ንፁህ የእገዚአብሄር ወንጌል እያገለገልክ ስላለህ እርሱ በማይጠፋው እና በከበረው የሕይወት አክሊለል ጌታ በአባቱ እና በመላእክቱ ደግሞም በቅዱሳን ፊት ያከብርሃል እኔ በአስተምህሮህ በጣም ነው ህይወቴ የተለወጠው እናም እነዴት ማገልገል እና መኖር እናዳለብኝ በደምብ አውቂያለው ወንድማችን ያሬድ እግዚአብሄር አሁንም ይባርክህ ይጠብቅህ ፊቱንም ያብራልህ !
አሜን አሜን አሜን 🙏🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ከጌታ ዘንድ የተቸርከን የተወደድክ ወንድማችን ያሬድ ከሁሉ በላይ የጊዜው የሆነውን መልዕክት የሰጠህን የቃሉን ባለቤት እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ለምትወዳት ሀገርህ መዋጋት ያለብህን ክፉውን አስተሳሰብ የሚገድለውን መንፈሳዊውን ጦርነት እየተዋጋህ ስለሆነ አንተንም ከልቤ በብዙ ተባረክ እላለሁ. በርታ!!
አሜን አሜን ጌታ በቃ ይበለን ጌታ ይባርክህ
አሜን አሜን ! አምላካችን ይችላል ሲልይሆናል አምናለሁ እናያለን ጸሎታችንን የሚሰማ በዙፋኑ አለ። ወንድሜ አንተም ቤትህም ተባረኩ ይብዛልህ።
አሜን!!! መዞር ያብቃ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ
በእውነት ይህንን ትምህርት በመላው ኢትዮጵያ ምድር ሁሉም በአንድነት ቁጭ ብሎ እቤት ውስጥ ፣ ወይ በሬዲዮ፣ ወይ በቲቪ ሳይሆን በቃ ከቤቱ ውጪ ወጥቶ በአንድነት ሰጥ ረጭ ብለው ይህንን ቢሰሙና በአንድነት ንስሀ ብንገባ እሱ ይቅር ባይ ነውና ይቅር ይለን ነበር ። ወገኔ ንቃ ለዚህች ለምታልፍ አለም የማያልፈውን ለልጆቻችን አናውርስ ። እረ ጌታ በቃችሁ ይላል😭😭😭😭😭😭እንስማው እንመለስ 🙏🙏🙏🙏ያሬዶ እግዚአብሔር ይባርክህ በድጋሚ
የተወደክ እግዚአብሔር ሰው ያሬዶ እንክዋን አደረሰህ መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇መዞር ይብቃን ። ኢትዮጵያ ማረፍን ትሻለች በቃን መዞር በቃን ዘረኝነት አንድ እንሁን ወደእግዚአብሔር እና ወደ ቃሉ እንመለስ 🙏🙏🙏የፍሬ ዘመን ዮሁንላቹ ለመላው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
የተወደድክ ውድ ወንድሜ ወንጌላዊ ያሪድ በዘመናት ሁሉ የከበረው የአምላከችን የእግዚአብሔር ታማኝ ባሪያ ዘመንህ ይባረክ አይኖችህን በልጅነትህ የከፈተ ማምለጥ ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን በሽህ እና በአስር ሽህ የሚቆጠሩትን እድታሰመልጥ እቃ ያደረገህ አገልጋይ ምንም የምለው ነገር በይኖረኝም ግን ተክክለኛ እይታ ብቻ ሳይሁን እውነታው ስለሆነ እግዚአብሔርን የናቁ ይናቃሉ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሕዝብ እንደ ቃሉ እግዚአብሔርም አያውቃቸውም። ባንተ እደተላለፈው መልዕክት ተሰፋችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን የሚያስብብበት ዘመን መጥቶል የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችንና መዳህገኘኒታችን ኢየሱሱ ክርቶስ ስም ትናንትናም ዛሬም ነገም ለዘለአለም በሰማይ በምድር በፍትረታት በጉዝም ይክበር ይባረክ።
አንተም የእግዚአብሔር ባሪያ ዘመንህ ውድ ባለቤት ልጆችህ አግልግሎትህ በእጥፍ የምትዘረጉበት ዘመብ ይሁንለህ።
በእርግጥ 25 አመታት የከበረውን እንቁ በአንተ ላይ አምላኬ የተከለው እያወራ ስለሆነ ከላፍክ በኋላ ሳይሁን አሁን በጣም እንደ ምንወድህና እንደመናከብርህ መመሰከር በእግዚአብሔር ፊት ክብር ነው።
ተባረክ የማታሳፍር የእግዚአብሔር ባሪያ
በአንት መቼም እንዴት እደምባረክ:: ጌታ እየሱስን እንድናውቅ የምታስተምር ተባረክ::ይሄንንም ወረቀት እስኪርብቶ ይዤ ነው የማየው🙏🙏🙏
🙏🙏
በእውነት የዘላለም አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ሁል ግዜ ከእውነት ጋር ስለምትቆም ዘመንህ ይባረክ ተባረክ
This is the most powerful message regarding my Ethiopia. Thank you Evangelist Yared!
ዋው ሥላንተ ጌታን እባርካለው ተባረክ መልካም አዲስ አመት ለመላው ቤተሠብህ
Amen Tebare
ወንድሜየ ያሬዶ, ጌታ ጸጋ ያብዛልህ ።
አሜን ይብቃ ወንጌላዊ ያሪድ በአንተ ብዙ ተምሬአለሁ እባክህን በአዲስ ኪዳን አማኞች በእግዚአብሔር መልአክት ይጠበቃሉ ወይስ ራሱ እግዚአብሔር ነው የሚጠብቃቸው ምክንያቱም አንድ ሰው እብራዊያን 1÷14ን ጠቅሶ የመልአክት ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው መዳንን ሊወርሱ ያሉት ናቸው እንጂ እኛ ድነናል ወርሰናል የሚል ስላስተማረ ነው አደራ በዚህ ጉዳይ አስተምረን።
በመላዕክትም ጠበቀን፣ በሰውም ጠበቀን ያው የሚጠብቀን እግዚአብሔር ነው። ዕብ. 1፥14 የሚናገረው ስለ አመንነው ስለ ሁላችን ነው። እኛ ድነናል፣ እየዳንን ነው፣ እንድንማለን። ክፍሉ የሚናገረው ወደፊት በጌታ መምጣት በሥጋ ትንሳኤ ስለ ምንድነው መዳን ነው። የጠቀስከው አስተምህሮ ስህተት ይመስለኛል።
@@EvangelistYaredTilahun አመሠግናለሁ ወንጌላዊ ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ በደንብ በዚህ ክፍል ላይ ብታስተምር ጥሩ ነው ብዙዎችም መረዳት ያገኛሉ።
Ameen Amen Amen
Amen amen
አሜን መዞር ይብቃን ጌታ ኢየሱስ ፀጋውን ያብዛልን ወንድሜ ያሬድ የጌታ ፀጋ ይብዛልክ
Tebarek wendme yehe tiyakye never zare temleseling abzito Egiz5 ybarkih
ወንጌላዊ ያሬድ ተባረክልን
እሜን ይብቃን ክፉ የማንሰማበትን ማዳኑን ብቻ የምናይበትን ዘመን ይሁንልን የመዞራችንን ሚስጥር ቁልጭ አድርገህ አሳይተህሕናል ጌታ እገልግሎትህን ዘመንህን ይባርክልህ ወንጌላዊ ያሬድ!
ወንድማችን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ የመልካም አዲስ አመት ከነቤተስብህ ይሁንልህ ይህን አፅናኝ ቃሉን የላከልን አምላካችን ይመስገን ቃሉ ሺህ ፍሬ እንዲያፈራ ወገኖቼ ላምላካችን እረፍት አንስጠው እንፀልይ እንጩህ እናልቅስ መልካም አዲስ አመት ለመላው ኢትዬጵያውያንእና ኤርትራውያን በሙሉ
አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ጌታ ይባርክ ወንጌላዊ ያሬድ አሜን እግዚአብሔር ይብቃ ይበለን
Wendim yared geta yibarkih.melkam Addis amet ke betesbeh gar
A touching and True message of God's time & Blessed is the Ture servant of God !!!
ውድ ወንድማችን ያሬድ የዘላለም አምላክ አብዝቶ ይባርክህ ___ ኢይጵያውያን ወገኖቼ ይህ ዙረት እንዲቆም ለውጥ ክራሳችን መጀመር አለበት __ በውአጣችን የተደበቀን ማንኛውንም አይነት የጨለማ ባህሪ ዛሬ እንቅበር __ ሁሉንም ዚጋ እናክብር እንውደድ ፤ መናናቅ አናቁም __ የዚያን ጊዜ የዘላለም አምላክ ይባርከናል ፤ ምድራችንንም በሰላም ያጥለቀልቃታል !!!
እጅግ በጣም እናመሰግናለን እንኳን አንተንም ከነቤተስብ በስላም አደርስህ መልካም አዲስ አመት ። እግዚአብሔር ሆይ ይህን አስተሳሰብ የምታመጣ አንተ ብቻ ስለሆንክ የሀገራችንን መሪዎች በፊትህ እናቀርባለን 🙏🙏
Amenn Be kerstos Eyesu sim yibkan.!!!
አሜን ይብቃ !ጌታ ይባርክህ የተወደደክ ወንድማችን ያሬድዬ
በአሜሪካ ያለከው የተወደድከው ወንድማችን ያሬዳ እንኩዋን አብሮ አደረሰን አሜን ይበቃኛል ጌታ እየሱስ ከነቤተሰብክ ይባርክህ
አሜን አሜን
ኦሪት ዘዳግም 2
3፤ ነዚ ኸረንዚ ምዛር ይኣኽለኩም፡ ንሰሜን ገጽኩም ተመለሱ። Amen 🙏🏽. Stay blessed Evangelist Yarde. Thank you
አሜን! እግዚአብሔር አገልግሎትህን አንተን ቤተሰብህን በብዙ ይባርክ!!! መልካም አዲስ አመት!!!!
E/r yibarkh wendim yared
Tebark tsegawen yabezaleh
Amen Yaredo Geta yebarkeh. Awo yebekal!!!!
Very wonderful, powerful, timely and earnest message ,Thank you pastor, God bless you
አሜን ጌታ ይርዳን::
እንኳን ለአዲስ አመት በሰላም አደረሰህ ከቤተብህ ጋር ወንደም ያሬድ.ተባረክ.🙏🏽💕
Omg wonderful message. ጌታ እየሱስ በአንተ ተጠቅሞ እንዴት እንደሚያስገርመኝ። በእኔ መንፈሳዊ ሂወት ትልቅ ቦታ አለህ ያሬድ መንፈሳዊ አባቴ። አሜን የተረገመውአስተሳሰብ ከሁላችን ውስጥ የሞተ ይሁን። መዞሩንም እግዚአብሔር አምላክ በቃችሁ ይበለን።
Amen Amen Beka Yebelne Mastewalen Abezalen
BLESS U. AMAZING MESSAGE.
እግዚአብሔር ይባርክህ :ዘመንህ ይባረክ በመልእክቱ ተገርሜአለሁ።
ተባረክ ለመላው ቤተሰብህ መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ ለምልም
ኦ አምላኬ በእየሱስ ስም ከኔ ትውልድ መዞር ይቁም እውነት ነው ዘመንህ ይባረክ ትምህርቶቹ ብዙ እማራለሁ፡፡
God Bless U !!!!!!!!!
አሜን አሜን ጌታ በቃ ይበለን ጌታ ይባርክህ ወ/ያሬድ
የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ይባርክህ !! አሁንም አሁንም ፀጋውን ይብዛልህ !! እኔ አንተን ካወቅሁህ ዓመት ጀምሮ እየጨመርክ እንጂ እንደ አንዳንድ አገልጋዮች እየወረድክና እየቀነስክ አልመጣህም፡፡
ክብር ሁሉ ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን!!!
አሜን!!! የተወደድህ ወንድማችን።
መልካም አዲስ አመት ።
እግዚአብሔር የምንማልድበትን የምንጸልይበትን አቅጣጫ አሳይቶናል አሜን መዞር ይበቃል! እንኳን አንተንና ቤተሰቦችህን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ!!!❤🌻🌻🌻
God Bless you brother Yared an excellent message!!Yes Ethiopia’s solution is only from our God!!!Let Him say is Enough!!!
አዘወትር ምህረቱና ቸርነቱ የማየልቅበት ምለካችን እግዚአብሔር ፣ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልኩኝ፣ ከሁሉም የሚበልጠውን እውነተኛ የእግዚአብሔርን ድምጽ በዚሁ ገጽ ለይ ለቅቄዋለሁና በማስተዋል አንብባችሁ ተጠቀሙበተ፣ ለወገኖችም እንድታደርሱልኝ በጌታ ፍቅር አሳስባለሁ፣ ተባረኩ።
Amennnnn yibkan Tebarke 🙌🙌
ወሳኝ ምክር እና ተግሳፅ ነው!!
እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ ወንድማችን ያሪ
መልካም ዓዲስ ዓመት ለአንተ እና ለመላው ቤተሰብህ።
Amen 🙏 This is the time!!!
እግዚአብሔር አባታችን አብዝቶ ይባርክህ መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻🌻🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Tebarek amen
አሜን ይብቃን እግዚአብሔር ሆይ በቃ በለን! ወንድሜ ያሬድ በብዙ ተባረክ መልካም አዲስ አመት ለአንተና ለቤተሰብህ ይሁን፡፡
Be Blessed
Wongelawi Yared, may God bless you to teach us on the subject no one dares to speak on, with the boldness the Lord has given you.
አሜን አሜን አሜን አሜን
Lib yeminka melket new geta yebarkh. Yehen hasb bedfret menger kelal aydelm yemenfeskudeus erdat selalbet new. Tebarek
ይህ መልዕክት መስከረም 2-1-2014 ዓ.ም. በሰሜን አዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክርስትያን ተተላልፏል፡፡ የምስራች፡- እግዚአብሔር በወንጌል ምደሪቷን የሚያጥለቀልቅ ተውልድ አስነስቷል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ፡፡
ወንድሜ ያሬድ እግዚአብሔር ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ መልካም አዲስ ከመላው ቤተሠብህ ጋር ይሁንላችሁ የሰላም የፍቅር የአንድነት የጤና ዘመን ይሁንልን በኢየሱስ ስም ::
ዘመንህ ይባረክ ያሬድ
እግዚአብሔር ይስጥልን እጅግ ድንቅ ትምህርት እድሜ ይስጥልን👏👏
ጥሩ በጣም ጥሩ ትምህርት ወቅታዊ ትምህርት : ቃለ ህይወት ያሰማን:: እችዚአብሄር ይባርልን::
እግዚአብሄር ይባርክልን::
ክብር ሁሉ ለሉኡል እግዚአብሔር አምላክ ይሁን አሜን፡ በጣም በጣም የተደነኩኝ ነው የሰማሁት እጅግ በጣም ደስ የሚል መሰረቱ ላይ ያለው ችግር ነው እግዚአብሔር የገለጠልህ፡ ግን ደስ የሚለው ነገር ጌታ በቃ ሲል ያበቃል፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንጌላዊ ያሬድ ተባረክልኝ 🙏🏽 እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ከነ ቤተሰቦችህ
Amen geta beqachu yibelen.
አሜን ይበቃል ይበለን
ጸጋ ይብዛልህ ያሬዶ
አሜንን አሜንን ጌታ ሆይ ይበቃኛል
አሜን አሜን አሜን ዘመነህ ይባረክ ያረዶ
Thank you yaredo ፀጋና ስላም ይብዛልህ!
Ameeeennn
Amen God bless you Brother.
Ewenet new yemitayewun liyunetachinin akbiren yemaytayewun andinetachinin magulat alebin, geta asteway lib yargilin.
ቸር ያሰማህ ጌታ እየሱስ ይባርክህ
አንተንና መላው ቤተሰብህንም ያሬዶዬ 🙏ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ከነቤተሰብህ🙏 አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን። 🙏🙏
Best insight and message. You never failed me in all your ministry. Happy New year to you and your families.
Thank you yaredo ….and happy new year to u and your family Stay blessed
Thank you too
አሜን በቃ ይበለን!
በትክክል
ያሬዶ አንተ የተባረክ ነህ ተባረክልን
ተባረክ ያሬድ
እንኳን አብሮ አደረሰን ወገኖች ተባረኩ ❤️🙏🇪🇹
እንኳን አብሮ አደረሰን ያሬዶ
You always teach us the Bible as if you don't know it you make it really beautiful and inspiring also make me dig more God bless you yardo!
You are so welcome
Amen amen God bless you my brother!!!
ኣምላኬ ኣምላኬ ኣስበን
አሜን ጌታ በቃ ይበለን
አሜን