ድክመቴ _ ሳሚ-ዳን / Dikmete _ Sami-Dan / New Ethiopian Music 2022
HTML-код
- Опубликовано: 31 янв 2025
- Song writer - Sami-Dan
Arranged by - Flashkiiddo
Mastering - SoundBetter ( Matty LA )
ድክመቴ
እንደብረት ማይሰበር በህይወት ትግል ማይረታ
በቃሉ እምነት የሚፀና በሰው ወሬ ማይፈታ
ሁሌ እንደቆምኩ ባንድ መስመር ምንም የለም ሚያስፈራኝም
ሳሳልፈው እንዳመጣጡ ስቀበለው ሁሉንም
አንዲት ክፍተት ሳላይ ኖሬ
አቅሜ ሳይደክም እስከዛሬ
አሁን ገና ተገመተ
ባንቺ ምክንያት ተከፈተ
ልቤን ዘልቀሽ ስትገቢበት
ያ ብርሀንሽ ቢሞቀኝም
ባጣትስ ብዬ ያልኩት ሀሳብ
ከፍርሀቴ አላዳነኝም
ድክመቴ አንቺ ብቻ ድክመቴ (2x)
ላንድ ነብሴ ነበር የምኖረው
ቢሞላም ባይሞላም የለም ምጨነቀው
ዝቅ ቢል ሰማዩ ከፍ ቢል ምድሩ
አይበርደኝ አይሞቀኝ ቢታመስ ሀገሩ
አንቺ ግን ስትመጪ ሁሉም ተቀየረ
ከኋላ ወደፊት የኔ አለም ዞረ
ድክመቴም ተገኘ የምዝልበት
ምክንያትም ተገኘ የምኖርለት
ሠው ሁሉ ያወራል ዛሬ ተደንቆ
የኔና ያንቺን ነገር ሁሉ አውቆ
ያ ግዴለሽነቴ አበቃ
የጨፈገገው ኑሮዬ ተነቃቃ
ድክመቴ አንቺ ሆንሺብኝ በቃ
እንዳላጣሽ ብዬ ቀን ማታ ጥበቃ
ድክመቴ አንቺ ሆንሺብኝ በቃ
ያ ግዴለሽነቴም በቃ አበቃ
ድክመቴ አንቺ ብቻ ድክመቴ (2x)
ፍቅር ገባ ቤቴ ዘንድሮ
ብርሀን ሞላው ፈካ የኔ ኑሮ
ዛል አልኩኝ በቃ ማበጥ ቀረ
እሷ ጋራ ልቤ ሄዶ ቀረ
ፍርሀት ሽው አለብኝ ጠብቆ
ባጣትስ ብሎ ልቤ ተጨንቆ
በፍቅር ጥላ ስር ተጠልዬ
እሷን እሷን እሷን ብቻ ብዬ
ድክመቴ አንቺ ብቻ ድክመቴ (2x)