Комментарии •

  • @adamuabegaz512
    @adamuabegaz512 5 лет назад +2

    ብሄራዊ እርቅና መግባባት እውን የሚሆነው ላለመግባባት የሆኑትን በመግባባት በሆኑ በመቀየር በአዲስ የህግ የበላይ በሚሆንበትን ህገ ህዝብ የሆነ አዲስ ህገ መንግስት ላይ በአንቀጽ በማስቀመጥ ለትውልድ ተሸጋጋሪ የሚሆን የህዝብ መተዳደሪያ ሰነድ ሕገ ኢትዮጵያ ማዘጋጀት ጊዜው አሁን ነው እያንዳንድ ፖርቲ ታዋቂ ግለሰቦች ለህገር እዲህ ይሁንልን የሚሉትን የያዘ አዲስ ህገመንግስት ከኢትዮጵያውያን በመነጨ የፍላጎታቸው ሀሳብ ያቀፈ የጋራ ኮንስትቲውሽን ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ሁሉም በአንድነት የሚያምን ማሰብ ያለበት ነው ።

  • @getachewtessema4064
    @getachewtessema4064 5 лет назад

    ስለ ብሔራዊ መግባባት ውይይት መልካም እንደነበር ታዝቤአለሁ
    ወያኔ የበታተናቸውን አንድነት ሙሁራን ፣ ሽማግሌዎች ፣ አስማሪዎች ፤-------
    ተማሪዎች ፣ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወያይቶበትና ፣ ተከራክሮ የተሻለ መፍትሔ ይመጣል የሚል ግምት አድሮብኝ ነበር ። ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ የገቡትም የኢትዮጵያን ሕመም መርምረው ይፈውሷታል የሚል ጉጉት አድሮብኝ ነበር ። ገና ከመግባታቸው እና ሥራውን ከመጀመራቸው በፊት ውዝግብ አስነስተው ሕዝባችንን ------ አስፈጅተዋል ።
    የፓለቲካ ፓርቲ ነንባዮች አስቀድመው የሚለወጥ ሕግመንግሥት አይኖርም ይሉናል ። የኢትዮጵያ ዋና ከተማና የብሔሮች መኖሪያ የሆነችውን አዲስ አበባን " ፊንፊኔ " ብለው በጉልበታቸው ስም
    ለጥፈውበታል ። ይህን የኢትዮጵያን ሕዝብ ያላሳተፈ የአንድ ፓርቲ ውሳኔ ሕገወጥና ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ።
    የወያኔ መንግሥት እና ተባባሪዎቹ የነበሩት " ክልል " ብለው ሀገር በመከፋፈል ሕዝብን አፋጅተዋል ። በየጎሳህና በምትናገሪው ቋንቋ ሂደህ ኑር ተብሎ ሕዝባችን ተመዝብሯል ሕይወቱንም ገብሯል ።
    ዛሬም የዚያው አስከፊ ሶቆቃ እንዲቀጥል የሚፈልግ ቡድን አለ ።
    የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነውና አስፈራርተው ሊሰለጥኑበት ይፈልጋሉ ።
    ያለፈውን የመሳፍንት ዘመን ፣ የፊውዳል ዘመንና የዲክቴተሮችን ታሪክ በመቆፈር ሕዝብን ያወናብዳሉ።
    ያለፈውን መጥፎ የሚሉትን ሳይለውጡትና የተሻለ ሥራ ሳያሳዩ ፣ በደፈናው መኮነንና ጥላሸት መቀባት የደካማነት ተግባር ነው ።
    በተለይም ወጣቱን በጠመመ ውሸት ማሳሳት የሰይጣን መንገድ ነው ።
    የታወቁትን ቲቪ እስቴሽን ፣ ሬዲዮ ጣቢያዎችንና ሶሻል ሚዲያን ማንቋሸሽ ፣ እኔ ብቻ ቅዱስ ነኝ ማለት የአምባገነኖች ባህሪያት ነው ። የዘር ፖለቲከኞችን በሕጋዊ መንገድ እንጋፈጣለን ። ዕውነትን
    ይዘን እንረታቸዋለን !