ስንቶቻችን ነን እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ወይም በእንተ እግዚተነ ማርያም 12 ግዜ በትክክል የምንለው ?ትርሙንስ?

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 10 фев 2022
  • ለምን ?? [12] ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና በእንተ እግዝእትነ ማርያም. እንላለን።
    ___________________________
    በቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት የኃጥያት ማሠሪያ ይፍታችሁ ሲል [12] ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና [12] ደግሞ በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላል። ካህናትና ምዕመናን በሙሉ በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህንኑ [12] ጊዜ እንላለን።
    እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት፦ አቤቱ ክርሰቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርሰቶስ ማረን ማለት ነው።
    አስራ ሁለት ጊዜ እግዚኦ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሌሊቱ 12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሠራነው ኃጥያት ለሃያአራቱ ፳፬ [24ቱ] ሰዓት ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ነው።
    ሌላው አሥራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት ፦
    ፩ኛ. በስመ ሥላሴ ነው። በእያንዳንዱ ፊደል
    _____________________________
    አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
    ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
    ____________________________
    ፪ኛ. የድኃነታችን ምክንያት በሆነችው በእመቤታችን ስም ፊደል
    _______________________________
    ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
    ፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
    _____________________________
    አቆጣጠሩም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደታች ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት [በትንሿ] ጣት ወደላይ ነው።
    _____________________________
    ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን።
    _____________________________
    መሐል ጣት ወደላይ ፦ ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን
    _____________________________
    በቀለበት ጣት ወደታች ስንቆጥር፦ ለፍርድ መምጣቱን
    ______________________________
    በትንሿ ጣት ወደላይ ስንወጣ፦ ደግሞ ሁላችንን በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።
    ______________________________
    በእንተ እግዝእትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ፦ ከትንሽ ጣት ወደ ታች ይጀመርና በጠቋሚ ጣት ወደላይ ይፈፀማል። ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን የሚያሳየን ምስጢር ነው።
    ______________________________
    ምንጭ ከመጽሀፈ አሚን ወሥርዓት የተወሰደ
    በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ ተፃፈ
  • РазвлеченияРазвлечения

Комментарии •