30 አመታት በ 30 ቀናት / 30 Days Before 30th🎂 " 30 አመት ሲሆንሽ ምን ታደርጊያለሽ?" Day 17/ ቀን አስራ ሰባት

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 19 мар 2024
  • ሶስት አስር ዓመታት……. ሶስት መቶ ስልሳ ወራት……ሰላሳ ዓመታት።
    ከልጅነት ወርቃማ ጊዜ፤ ከወጣትነት ብርቱ ዘመን፤ ወደ ጉልምስና መሻገርያ ድልድይ….
    ከቤተሰብ የጋራ ህይወት፣ እስከ ወጣትነት የስራና የትምህርት ጊዜ፣ ወደ ሃላፊነት መደላደያ መንገድ።
    ይህንን ጊዜ……..ይህንን ዘመን……ይህንን ወቅት…….ይህንን ጉዞ ላስቃኛችሁ ነው።
    ቃልኪዳን ዘካርያሰ እባላለሁ። ተዋናይ፤ የፊልም ባለሞያ፤ ሚስት እና እናት ነኝ።
    ከአንድ ወር በኋላ….ከሳላሳ ቀናት በኋላ ሰላሳ ዓመት ይሆነኛል። የእድሜን አንድ እርከን እሻገራለሁ። ታድያ ይሄ ምን ጉዳይ ነው? ይሄ ምን ይገርማል? ወይም ይሄ ምን ይደንቃል? ካላችሁ።
    ብዙ ይደንቃል፣ ብዙ ይገርማል…ምክንያቱም
    ብዙ ትዝታ፣
    ብዙ ትዝብት
    ብዙ ደስታ
    ብዙ ሀዘን
    ብዙ ስራ
    ብዙ ህልም
    አለበት።
    ይሄ ይደንቃል፣
    ይሄ ይገርማል።
    በሁላችንም ህይወት ውስጥ ያለውን፣ ተነገሮ የማያልቀውን የህይወት ትዝብት በዚህ አጭር በሚመስል ጊዜ ያሳለፍኩትን፣ የኖርኩትን፣ የተመኘሁንት፣ ያሳካሁንት እና ያላሳካሁትን….ላወጋችሁ ነው። ላጋራችሁ ነው- በየቀኑ ለሰላሳ ቀናት።
    ነገር ጉዞው የጋራችን ነው። እኔ ሳካፍላችሁ እናንተም ትዝታችሁን ፣ ምኞታችሁን እና ህልማችሁን እንድታካፍሉኝ እጋብዝላሁ።
    አብራችሁኝ ሁኑ።

Комментарии • 7